1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቆሻሻ ክምር መደርመስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር መጨመሩ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 5 2009

በአዲስ አበባ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፣ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለዓመታት የተከመረ የቆሻሻ ተራራ ከትናንት በስቲያ ተደርምሶ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ። በአደጋው የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 65 ከፍ ማለቱ ተገልጿል።ጉዳት የደረሰባቸው 37 ሰዎች ባካባቢው ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እንደተደረገላቸው ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/2Z6av
Äthiopien Erdrutsch in einer Mülldeponie in Addis Abeba
ምስል DW/Y. G. Egziabher

በርግጥ የሟቾች ቁጥር ፣ አንድ የአገር ውስጥ መገናና ብዙኃን ያወጣው ዘገባ እንደሚያሳየው፣ 65 ነው ቢባልም፣ ያካባቢው ነዋሪዎች ቁጥሩ ከዚህ በላይ መሆኑን ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። የአደጋው መንስዔ እስካሁን በግልጽ ያልታወቀ ሲሆን፣ መሰነጣጠቅ የሚታይበት የቆሻሻው ክምር እንደገና ሊደረመስ እና ተጨማሪ አደጋ ሊያደርስ ይችላል በሚል ያካባቢው ነዋሪዎች ስጋት አድሮባቸዋል። 

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር  

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ