1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በበርሊን የጀርመን አይሁድ ጋዜጣ መታተም መጀመሩ፣

ዓርብ፣ ጥር 4 2004

በጀርመን ሀገር በተደላደለው የዴሞክራሲ ሥርዓት በመጠቀም፤ ያገሩ ተወላጆች ብቻ ሳይሆኑ፤የውጭ ተወላጆችም በራሳቸው ቋንቋ ፤ ጋዜጣ መጽሐፍ ና መጽሔት ማሳተም ራዲዮና ቴሌቭዥን አቋቁመው ማሠራጨት ይችላሉ።

https://p.dw.com/p/13jX8
የአይሁድ ማኅበረሰብ በበርሊንምስል picture-alliance/dpa

በጀርመን ሀገር የሚኖሩ፤ ሩሲያውያን፤ ሰርቢያውያን ፣ ፖርቱጋላውያን እስፓኛውያን እንዲሁም ጣልያኖች ሁሉም በየቋንቋቸው የሚታተሙ ጋዜጦች አሏቸው። በተለይ  በጀርመን  ሀገር ከሚኖሩት የውጭ ዜጎች መካከል በቁጥር ላቅ ያሉት ቱርካውያን ቢያንስ 7 ጋዜጦች ለህትመት ያቀርባሉ። በዚህ ላይ በእንግሊዝኛና  በፈረንሳይኛ ም የሚቀርቡ አያሌ ጋዜጦችና መጽሔቶች ለፈላጊዎች በሰፊው ይቀርባሉ። ከሰሞኑ ደግሞ እንደዘገበልን፤ «ጂዊሽ ቮይስ» የአይሁድ ድምፅ ፤ የተሰኘ ጋዜጣ መታተም  መጀመሩን ከበርሊን ፣ ይልማ ኃ/ሚካኤል የላከልን ዘገባ ያስረዳል።