1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቢሾፍቱ የሞቱት ጉዳይ

ረቡዕ፣ መስከረም 25 2009

ጎሜሽ የአውሮጳ ህብረት በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በዝምታ ከማለፍ እንዲቆጠብም አሳስበዋል ።

https://p.dw.com/p/2Qtob
Äthiopien Unruhen
ምስል Getty Images/AFP/Z. Abubeker

Beri.Brussels ( EP mp request for indpendent inquriy on the Bishoftu killing) - MP3-Stereo

ባለፈው እሁድ በቢሸፍቱ በእሬቻ በዓል የሞቱት ሰዎች ጉዳይ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ሽትራስቡርግ ፈረንሳይ በመካሄድ ላይ ባለው የአውሮጳ ፓርላማ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተጠየቀ ። ጥያቄውን ያቀረቡት በ 1997 የተካሄደው የኢትዮጵያ ምርጫ የአውሮጳ ህብረት ታዛቢ እና በአውሮጳ ፓርላማ የፖርቱጋል ሶሻሊስት ፓርቲ ተወካይ አና ጎሜሽ ናቸው ። ትናንት በጉባኤው ሂደት ጣልቃ በመግባት ጥያቄውን ያቀረቡት ጎሜሽ የአውሮጳ ህብረት በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በዝምታ ከማለፍ እንዲቆጠብም አሳስበዋል ። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ