1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቩርስቡርግ የባቡር ጥቃት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 12 2008

በደቡብ ጀርመን፣ በባቫሪያ ግዛት በምትገኘው በቩርስቡርግ እና በትሮይሽትሊንገን ከተሞች መካከል ሲጓዝ በነበረ አንድ ያካባቢ የመንገደኞች ማመላለሺያ ባቡር ላይ ትናንት ምሽት አንድ ወጣት በመጥረቢያ እና በጩቤ በጣለው ጥቃት በርካቶች ቆስለዋል።

https://p.dw.com/p/1JSCL
Schwerverletzte bei Attacke in Zug bei Würzburg
ምስል picture-alliance/dpa/K.-J. Hildenbrand

[No title]

ከአፍጋኒስታን የመጣ ተገን ጠያቂ ነው የተባለው አጥቂ በፖሊሶች መገደሉን የባቫሪያ ሀገር አስተዳደር ሚንስቴር ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ጥቃቱ ከሽብርተኝነት ጋር የተያያዘ መሆን አለመሆኑ በወቅቱ ምርመራ በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ ያካባቢው ፀጥታ ባለስልጣናት ገልጸዋል። ባቡር ውስጥ ስለተጣለው ጥቃት፣ ስለ አጥቂው እና ስለምርመራው በርሊን የሚገኘውን ወኪላችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬው ነበር። በመጀመሪያም የጠየቅሁት የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች አሁን በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ነው።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ