1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በተስፋ የሚጠበቀው የደ/ሱዳን ተቀናቃኞች ግንኙነት

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 30 2006

በደቡብ ሱዳን ካለፈው ታህሳስ ወር ወዲህ በመንግሥቱ ጦር እና በዓማፅያኑ መካከል በቀጠለው ውጊያ ስቃይ ውስጥ ያለው ተፈናቃዩ ሲቭል ሕዝብ ወደ የማሳው በመለስ ዘር እንዲዘራ እና ወደ ዕለታዊ ተግባሩ እንዲመለስ ለማስቻል በምሥራቅ

https://p.dw.com/p/1Bvu4
ምስል Reuters

አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ሸምጋይነት በሳምንቱ መጀመሪያ የአንድ ወር የተኩስ አቁም ስምምነት ደርሰዋል። ያም ቢሆን ግን ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል። በነገው ዕለት የሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች መሪዎች ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር እና የቀድሞ ምክትል ፕሬዚደንት ሪየክ ማቸር በአዲስ አበባ የሚገናኙበት እና የሚደራደሩበት ሁኔታ ይህንኑ ውጊያ ያበቃ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

ጌታቸው ተድላ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ