1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቱርክ የሩስያ አምባሳደር ተገደሉ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 11 2009

ቱርክ አንካራ ከተማ ዉስጥ በሩስያ አምባሳደር ላይ በተጣለ ጥቃት ተገደሉ። የ 62 ዓመቱ አምባሳደር አንድሪ ካርሎቭ በቱርክዋ ርዕሰ መዲና አንካራ ዉስጥ አንድ የፎቶ አዉደ ርዕይ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ ሳሉ ነዉ ከአንድ ግለሰብ በተቃጣ የሩምታ ተኩስ የተገደሉት።

https://p.dw.com/p/2UZ0m
Türkei Russischer Bootschafter Andrey Karlov während Ausstellungsrede in Ankara angeschossen
ምስል picture alliance/dpa/AA

 

አምባሰደሩ ጥቃቱ እንደደረሰባቸዉ ለሕክምና ወደ ሆስፒታል እንደተወሰዱና የሕክምና አገልግሎት ማግኘታቸዉ ቢዘገብም ጤንነታቸዉ በምን ደረጃ ላይ እንደሆነ አልተነገረም ነበር። «RIA» የተሰኘዉ የሩስያ የብዙኃን መገናኛ የዉስጥ የመረጃ መንጮችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበዉ ደግሞ አምባሳደር አንድሪ ካርሎቭ ለሕክምና ሆስፒታል ከደረሱ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ሕይወታቸዉ ማለፉን አረጋግጦል።  የተለያዩ የቱርክ መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸዉ ታጣቂዉ በኤግዚቢሽኑ ዉስጥ ባደረሰዉ የእሩምታ ተኩስ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ተጎድተዋል። በአንካራ ከተማ ሳካያ በሚል አካባቢ በሚገኘዉ በታዋቂ የ«ሳጋዳስ ሳንታላር ማርኪዚ» የኤግዚቢሽን ማዕከል «ሩስያ በቱርክ እንዴት ትታያለች » የሚል ርዕስን የያዘዉ የፎቶ አዉደ ርዕይ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ የሩስያን ጨምሮ በርካታ አምባሳደሮች ተገኝተዉ እንደነበር ተዘግቦአል። የቱርክ ባለሥልጣን ቢሮ እንደገለፀዉ ጥቃት አድራሹ ግለሰብ አንድ የአንካራ ፖሊስ ነዉ። ግድያ የፈፀመዉም ለሥራ የተሰጠዉ ሽጉጥ ነዉ። በኤግዚቢሽን ማዕከሉ የነበሩ የደኅንነት ሠራተኞች እንደተናገሩት ግለሰቡ በሩስያዉ አምባሳደር አንድሪ ካርሎቭ ላይ የሩምታ ተኩስ የከፈተዉ በአዉደ ርዕዩ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ የሚያደጉትን ንግግር እንዳበቁ  ነዉ። ቢያንስ ለስድስት ጊዜ ሳይተኩስባቸዉ አልቀረም።   

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ