1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በታላቁ ቦክሰኛ ሞሐመድ አሊ ሞት ዓለም ኃዘኑን እየገፀ ነዉ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 27 2008

ታላቁ የቦክስ ስፖርተኛ ሞሐመድ አሊ በትናንት ምሽት በፌኒክ አሪዞና በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። በቦክስ ውድድር 'ታላቁ' ለመባል የበቃው ሞሐመድ አሊ 56 ውድድሮች ያሸነፈ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 37 ተጋጣሚዎቹን በዝረራ ረትቷል።

https://p.dw.com/p/1J0dt
USA Boxer Muhammad Training in Florida
ምስል picture alliance/ZUMA Press/J. Joffe

ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በቦክስ ስፖርት ውድድሮች ካስመዘገባቸው አስደናቂ ድሎች ባሻገር በአፍሪቃ አሜሪካውያን የሰብዓዊ መብት ትግል ባደረገው አስተዋጽዖ የሚወደሰው ሞሐመድ አሊን ከደቡብ አፍሪቃዊው የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ እና ከአሜሪካዊው ማርቲን ሉተር ኪን ጁኒየር ጋር አነጻጽረው አሞካሽተውታል።

Boxer Muhammad Ali
ምስል picture-alliance/abaca

ሞሐመድ አሊ በቪየትናም ጦርነት አልዘምትም በማለቱ ለሶስት ዓመታት ከቦክስ ውድድር እንዳይሳተፍ ታግዷል። በቦክስ ውድድር 'ታላቁ' ለመባል የበቃው ሞሐመድ አሊ 56 ውድድሮች ያሸነፈ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 37 ተጋጣሚዎቹን በዝረራ ረትቷል።

በዩናይትድ ስቴትስ ልዊቭል የተወለደው ካሴስ ማርሴለስ ክሌይ ጁኒየር የእስልምና እምነትን ተቀብሎ ስሙን ወደ ሞሐመድ አሊ የቀየረው በጎርጎሮሳዊው 1964 ዓ.ም. ነበር። ፕሬዝዳንት ባራክ ኦቦማ ለፍትሐዊነት እና ሐይማኖታዊ መቻቻል ታግሏል ያሉት ሞሐመድ አሊ የታገለው «ለእኛ» ነው ሲሉ ተናግረዋል። ፓርኪንሰን ከተሰኘው የነርቭ በሽታ ጋር ለዓመታት ሲታገል የቆየው ሞሐመድ አሊ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው በ74 ዓመቱ ነው።

እሸቴ በቀለ

አዜብ ታደሰ