1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በታንጋኒካ ሃይቅ አስገራሚዉ ጀልባ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 10 2005

በታንጋኒካ ሃይቅ ከመቶ አመት በላይ እድሜን ያስቆጠረዉ አስገራሚዉ ጀልባ ይላል ሰምወኑን በዶይቼ ቬለ የባህል ድረ-ገጽ ካስነበባቸዉ ጽሁፎች መካከል፤ የለቱ ዝግጅታችን በታንጋኒካ ባህር ላይ ስለሚገኘዉ የጀርመን መርከብ ታሪክና እና በዉጭ አገር ተማሪዎች ዘንድ ተወዳጅ ስለሆነዉ የጀርመን ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ቅንብር ይዘናል።

https://p.dw.com/p/18Iir
Liemba ferry on Lake Tanganyika plying the route between Mpulungu Zambia Kigoma Tanzania SMO. FREE to download and use! (c) Simon Collins http://mirror-uk-rb1.gallery.hd.org/_c/travel/_more2002/_more11/Liemba-ferry-on-Lake-Tanganyika-plying-the-route-between-Mpulungu-Zambia-Kigoma-Tanzania-SMO.jpg.html?sessionVar=spider&sessionVarLocale=de
ምስል Simon Collins

ታሪኩ  የሚጀምረዉ ከመጀመርያዉ ዓለም ጦርነት በፊት በጎ አቆጣጠር ከ1913 ዓ,ም በጀርመኑ ንጉስ ቪልሄልም ዘመን  ጀምሮ በታንዛንያ ስለሚገኝ አንድ የጀርመን መርከብ መርከብ ነዉ። ይህ እስከዛሪ በታንጋኒካ ባህር ላይ የሚቀዝፈዉ የጀርመኑ መርከብ ከመቶ ዓመት በላይ እድሜን አስቆጥሮአል። የጀርመኖችን የቅኝ ግዛት ታሪክ ይዞ ሁለተኛዉን የዓለም ጦርነት ታሪክ ጽፎ፤ እድሜዉ ዛሪ ላለንበት በግሎባላይዜሽኑ ማለት ለአጥናፋዊዉ ትስስር ዘመን በቅቶ ዛሪም ከመቶ አመት በፊት እንደታሰበለት ተግባሩ በመካከለኛዉ አፍሪቃ በሚገኘዉ ሃይቅ ላይ ሰዎችን በመጓጓዝ ተግባሩን ቀጥሎአል። 

Die historische Aufnahme zeigt das Schiff «Liemba» aus dem Jahr 1913 auf der Meyer Werft in Papenburg. Niedersachsen will sich bei der Bundesregierung für die Modernisierung des Schiffs einsetzen. Das sagte ein Sprecher der Landesregierung am Donnerstag (25.03.2010) und bestätigte einen Bericht der «Neuen Osnabrücker Zeitung». Das Schiff «Liemba» war in Einzelteile zerlegt und in das damalige Deutsch-Ostafrika gebracht worden. Es ist auch in dem Hollywood-Klassiker «African Queen» mit Humphrey Bogart und Katharine Hepburn zu sehen. Ein Privatmann aus Papenburg möchte das Schiff wieder zurück nach Deutschland holen. Foto: Meyer Werft dpa/lni +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture alliance/dpa

ከረጅም ዘመናት ጀምሮ ግዙፉ የፊልም ኢንዱስትሪ ሆሊዉድ ጀርመናዉያንን የእኩይ መንፈስ መገለጫዎች አድርጎ ያቀርባቸዋል ።  በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1951 ዓ,ም የሆሊዉዶቹ የፊልም ተዋንያን ሃምፍሪ ቦጋርት እና ካትሪን ሄቡርን   «AFRICAN QUEEN»በተሰኘዉ በታንጋኒካ ሃይቅ በተሰራው የተሳካ ፊልማቸው ላይ ባላጋራ ሆና የምትቀርበው፣ የጀግና ተጻራሪ  ባህሪይ የተሰጣት ንግስት ሉዊዛ የተባለችው ናት ። በርግጥ ስሙ እንደሚያመለክተው የልዑላዊ ቤተሰብ አባል የሆነች ሴት ወይዘሮ  አይደለችም ። እዚህ ላይ ስሙ የተሰጠው ለመርከብ ነዉ።

በፊልሙ ላይ የሚታዩት ሁለቱ ዋና ገጸ-ባህርያት ጥንዶች፤ መርከቢቱን ያሰምጧታል። በርግጥ ይህች የጀርመናዉያን መርከብ ከታንዛንያ ጋር ምን አይነት ግንኙነት ይኖራት ይሆን? 

Geschützmannschaft auf dem deutschen Dampfer Graf Götzen im Oktober 1916 auf dem Tanganyika See in der Nähe von Uvira. Dieses 10.5cm/40 SK L/40 Geschütz stammt von SMS Königsberg.Diese Bild- oder Mediendatei ist gemeinfrei, weil ihre urheberrechtliche Schutzfrist abgelaufen ist. Dies gilt für die Europäische Union, die Vereinigten Staaten, Australien und alle weiteren Staaten mit einer gesetzlichen Schutzfrist von 70 Jahren nach dem Tod des Urhebers. http://de.wikipedia.org/w/index.php?title=Datei:Graf_Goetzen_Kanone.jpg&filetimestamp=20100331151112
ምስል cc

በሆሊዉዱ ፊልም ላይ «AFRICAN QUEEN» የሚል ስያሜ  የተሰጣት በታንጋኒካ ሃይቅ ላይ የምትገኘዉ ግዙፏ መርከብ በጎ,አ በ1913 ዓ,ም  በሰሜናዊ ምስራቅ ጀርመን በኒደርዛክሰን ግዛት ኤምስ ላንድ አዉራጃዉስጥ በሚገኘዉ ፓፕንበርግ በተባለ ቦታ ነበር የተሰራችዉ።  በጀርመኑ ንጉስ በዊልሄልም ዳግማዊ ትዕዛዝ የተሰራችዉ እና የቅኝ ግዛት ታሪክን የያዘችዉ ይህች መርከብ በዚያን ግዜ «ግራፍ ጎትዝን» Graf Götzen የሚል ስያሜ ተሰጥቶአት ነበር።

የጀርመኑ ንጉስ ዊልሄልም ዳግማዊ መርከቧ  እንድትሰራ ያዘዘዉ  በታንጋኒካ ሃይቅ ዳርቻ ከብሪታንያ እና ቤልጂየም ድንበር ለመለየት፤   የጀርመንን የቅኝ ግዛት ክልል አጉልቶ ለማሳየት ነበር።  ጀርመናዉያኑ ተቀናቃኞቻቸዉን ብሪታንያዉያኑን እና ቤልጂጎችን በልጦ ለመገኘት ብቻ ሳይሆን የአካባቢዉን ነዋሪንም ቀልብ ለመሳብ አስበዉ ነበር ይህን መርከም ለመስራት የበቁት። መርከብዋ እንድትሰራ ታዞ  ከተሰራች በኋላም Gustav Adolf Graf von Götzen የሚል የመሳፍንት ስም ተሰጥቶአታል።  ጀርመናዊዉ Gustav Adolf Graf von Götzen በጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር በ1900 አመታት መጀመርያ በጀርመን ቅኝ ግዛት ስር የነበረዉ የምስራቅ አፍሪቃ አካባቢ ከንቲባ እንደነበር ተጠቅሷል። የአካባቢዉ ነዋሪዎች በ1905 እና 1907 ዓ,ም ፤ አሁንም በጎ አቆጣጠር ነዉ፤ ጀርመናዉያን ቅኝ ገዥዎችን በመቃወም  «ማይ ማይ» የሚል  አመጽ አስነስተዉ ባካሄዱት ትግል ብዙ ደም ፈሶ በጀርመኑ መስፍን ድል አድራጊነት አመጹ ተቀጭቷል ። 

Dampfer Graf Goetzen Plakat African Queen. Filmplakat mit Humphrey Bogart und Katharine Hepburn 1951.

የጀርመኑ መስፍን አመጹን ካሸነፈ በኋላ አካባቢዉ እረጭ አለ፤  መርከቢቱም ከጦርነት መገልገያነት ወደ ሰዉ እና እቃ ማመላለሻነት ጥቅም ላይ ዋለች። ግን ይህች መርከብ በዝያን ዘመን ከተሰራችበት ከሰሜናዊ ምስራቅ ጀርመን ተነስታ በመካከለኛዉ አፍሪቃ ወደሚገኘዉ ታንጋኒካ ሃይቅ እንዴት ለመድረስ ቻለች? በሰሜናዊ ምስራቅ ጀርመን ፑፕንበርግ ከተማ መርከቡዋ ከተገነባች በኋላ ታንጋኒካ ሃይቅ ለማድረስ ከባድ በመሆኑ እንደገና መርከቧ በመልክ መልክ ተቆራርጣ፤ በ5000 ሳጥን ታሽጋ በእቃ ማመላለሻ መርከብ ወደ ምስራቅ አፍሪቃ አቅጣጫ የጀርመን ቅኝ ግዛት መዲና ወደ ነበረችዉ ወደ ዳሪሰላም ትላካለች። 1200 ቶን እንደሚመዝን የተነገረለት  ቁርጥራጭ  የመርከቢቱ ክፍል ከዳሪሰላም ከተማ ታንጋኒካ ሃይቅ 30 ኪሎ ሜትር እስኪ ቀረዉ ድረስ በባቡር ተጭኖ፤ ከዝያም ማመላለሻ ስለሌለ፤  በሰዉ ሸክም ሃይቁ ዳርቻ ድረስ ለመጋዝ መብቃቱ ተዘግቦአል።

በዝያን ግዜ ይህን የመርከብ ቁርጥራጭ ታንጋኒካ ሃይቅ ዳርቻ ላይ ሲገጣጥም የነበረዉ ጀርመናዊ ለቤተሰቦቹ በጻፈዉ ደብዳቤ «ስራዉ ጥሩ እየሄደልኝ ነዉ ጠንካራ የሆኑ 20 ህንዳዉያን  እና 150 ጥቁር    ሰራተኞች እያሰራሁ ነዉ፤  በርግጥ የመገጣጠሙን ስራ ስጀምር ደግሞ ተጨማሪ 100 ጥቁር ሰራተኞች ሳያስፈልገኝ አይቀርም» ሲል መጻፉ ተነግሮአል።  

Dampfer Goetzen Tanganjikasee / Foto 1. Weltkrieg / Krieg in den Kolonien: Deutsch-Ostafrika (heute Tansania). - Dampfer "Goetzen" im Bau in Kigoma, Tanganjika-See. - Foto, 1914. picture-alliance / akg-images
ምስል picture-alliance/akg-images

መርከቢቱ ተገጣጥማ ስታበቃ ታድያ አካባቢዉ ላይ በቅኝ ግዛት ሰፍረዉ የሚገኙት ብሪትናዉያን እና ቤልጂጎች በስራዉ ተደንቀዉ አይናቸዉን ማመን ነበር ያቃታቸዉ።

መርከቡ እንደተገጣጠመ የአንደኛዉ አለም ጦርነት በመቀስቀሱ በመስፍን ስም የምትጠራዉ መርከብ ማለት « ግራፍ ጎትዘን» ከብሪትኑ እና ቤልጂጎች ጋር መዋግያ የጥይት መከላከያ እና ፈንጂን አመላልሳለች። ይህ ታሪኳ ነዉ ታድያ ለሆሊዉዱ የፊልም ኢንዱስትሪ «AFRICAN QUEEN» በተሰኝ አዲስ ታሪክ በፊልም የተቀረጸላት። በርግጥ ፊልሙ የጀርመናዉያኑን ስራ አጉድፎ ያሳያል። 

በጎርጎርሳውያኑ አቆጣጠር 1916 ዓ,ም ጦርነቱ በየብስ ላይ ተባብሶ በመቀጠሉ፤ ጀርመናዊዉ የመርከቢቱ ሰሪ፤ መርከቢቱ ጠላት እጅ ከምትወድቅ በማለት ታንጋኒካ ሃይቅ ዉስጥ እንድትሰምጥ አድርጓል።  

«GRAF VON GOETZN» የሚለውን የአንድ ጀርመናዊ መስፍንን ስም ያነገበችዉ መርከብ ግን ሰምጣ አልቀረችም። የአንደኛዉ የዓለም ጦርነት እንዳበቃ ቤልጂጎች መርከቢቱን ከሰመጠችበት አዉጥተዉ «ሊይምባ» የሚል ስም ሰጥተዉ ለስራ አሰማርዋት። ከአንዳንድ ግዜ ብልሽት በስተቀር ከመቶ አመት እድሜ በላይ ያስቆጠረችዉ በጀርመን የተሰራችዉ መርከብ፤ መጀመርያ ጀርመናዉያን ለሰዉ ማመላለሻነት እንዲሆን እንደሰሯት፣ አሁንም ከመቶ አመት በላይ በታንጋኒካ ሃይቅ 673 ኪሎ ሜትር ርዝመት እየቀዘፍች ሰዉ እና እቃን በማመላለስዋ  ትታወቃለች። 

የታንጋኒካ ሃይቅ በመካከለኛዉ አፍሪቃ የሚገኝ ረጅም ርዝመት ያለዉ ሲሆን በዓለማችን ከሚገኝ ሃይቆች መካከል በርዝመት ስድስተኛ  በጥልቀት ደግሞ ሁለተኛ ነዉ።

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ