1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቴህራን የብሪታኒያ ኤምባሲ ጥቃትና መዘዙ

ረቡዕ፣ ኅዳር 20 2004

ኢራናውያን ተቃዋሚዎች ቴህራን የሚገኘውን የብሪታኒያ ኤምባሲ ትናንት ጥሰው መግባታቸውና ጉዳትም ማድረሳቸው በዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ተወግዟል ።

https://p.dw.com/p/RzU8
ተቃዋሚዎች በኤምባሲምስል dapd

ብሪታኒያ ዛሬ ዲፕሎማቶቿን ከቴህራን ያስወጣች ሲሆን ተቃዋሚዎቹ ለወሰዱት እርምጃም የኢራን መንግሥት ተጠያቂ ነው ስትል ከሳለች ፤ ቴህራን ከባድ መዘዝ ሊከትልባት እንደሚችልም አስጠንቅቃለች ። ኤምባሲዋም ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚዘጋ አስታውቃለች ። ኢራንም ለንደን የሚገኘውን ኤምባሲዋን እንድትዘጋ ተነግሯታል ። ኖርዌይ ደግሞ ቴህራን የሚገኘውን ኤምባሲዋን ዘግታለች ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ