1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በነፋስ ኃይል የሚሠራ የኤልክትሪክ ማመንጫ መሳሪያ የፈለሰፈው የማላዊው ወጣት፣

ሰኞ፣ ሐምሌ 20 2001

የዓለም ጥንታዊ ሥልጣኔ ሀ ተብሎ ሲጀመር ፣ ግንባር ቀደም ቦታ ይዞ የነበረው አፍሪቃ፣«ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ » እንደተባለው፣ በተለያዩ ምክንያቶች ከሌሎቹ ክፍለ ዓለማት ሁሉ በሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ኋላ ቀር የመሆን መጥፎ ዕጣ የገጠመው ይመስላል።

https://p.dw.com/p/IyKA
በድህነት ሳቢያ ከውጭ የአህል እርዳታ ለሚጠብቀው የማላዊ ህዝብ ፣ ሳይንስና ሥነ -ቴክኒክ ምን ዓይነት መፍትኄ ያስገኝ ይሂን!?ምስል picture-alliance/ dpa/dpaweb

ዓለም አቀፍ ዝና ያተረፉት ዕውቁ ናይጀሪያዊ ኢንጅኔር የኮምፒዩተር ሳይንቲስትና የስነምድር ምርምር ሊቅ ፊሊፕ ኢማጋዋሊ፣ በመካከላኛው ክፍለ-ዘመን አፍሪቃውያን ለባሪያ ፍንገላ የተዳረጉት፣ በሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ተበልጠው በመገኘታቸው ነውና ሁለተኛ ዙር ውርደት ሳያጋጥማቸው ሳይንስንና ሥነ-ቴክኒክን የሙጥኝ ሊሉ ይግባል ሲሉ ይመክራሉ። ግራም ነፈሰ ቀኝ ፣ ቀጣዩ ዘገባ ፣ የፈጠራ ውጤት፣ የአሰፈላጊ ጉዳይ ግፊት መሆኑን የሚያስገነዝብ ሲሆን ፣ አንድ የማሊዊ ተወላጅ የሆነ ወጣት በ 14 ዓመቱ ፣ የፈጠራ ውጤት ባለቤት በመሆን የሥነ- ቴክኒኩን ዓለም ያስደመመበትን ሁኔታ፣ ሐና ደምሴ እንደሚከተለው ታቀርበዋለች።

ሐና ደምሴ/ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ