1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በናይጀርያ አፈንጋጭ ሀገረ-ገዢዎች ግንባር ፈጠሩ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 21 2006

የናይጀርያ ገዥዉ ፓርቲ የህዝባዊ ዲሞክራቲክ ፓርቲ በእንጊሊዘኛ አፅህሮቱ PDP አዲስ የፖለቲካ ፈተና ገጥሞታል። የገዥዉ ፓርቲ አባላት የነበሩ ሰባት ሀገረ ገዥዎች ከፓርቲያቸዉ አፈንግጠዉ፤ All Progressives Congress (APC በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ) ከተሰኘዉ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ ጋር የጋራ ፓርቲ መስርተዋል።

https://p.dw.com/p/1AR3v
Auf dem Bild: Menschen Protestieren in Abuja, Nigeria gegen Wahlfälschung. Foto: Uwais Abubakar Idris / DW am 28.11.2013.
ምስል DW/U.Abubakar Idris

እነዚህ ከገዥዉ ፓርቲ አፈንግጠዉ የወጡት ሀገረ ገዥዎች የመንግስት ተቃዋሚ ፓርቲን ተቀላቀሉ ማለት፤ ሀገሪቱን ከሚመራዉ የፖለቲካ ፓርቲ በበለጠ ተቃዋሚ ፓርቲ በሀገሪቱ ምክር ቤትም ከፍተኛ አባላት ቁጥር አላዉ እንዲሁም፤ የሀገሪቱንም አብዛኛዉን ክፍል ተቆጣጥሮ ይገኛል። በእንግሊዘኛ አፅህሮቱ APC በመባል የሚታወቀዉ ዋንኛ ተቃዋሚ ፓርቲ፤ አዲሶቹ ሹማምንት ሲቀየጡት ከአፍሪቃ ትልቁ ፓርቲ መሆኑም የፓርቲዉ መሬዎች በኩራ ይገልፃሉ። ለዚህ ፓርቲ እንቅስቃሴ ዓላማዎች መካከከል የፓርቲዉ ዋና ተቀናቃኝ የሆኑት የሀገሪቱ ፕሪዚዳንት ጉድ ላክ ጆናታን በጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ,ም ዳግም እንዳይመረጡ ለማድረግም እንደሆን ተነግሮአል። በዚሁ ጉዳይ ላይ የዶቼ-ቬለዉ ሳም ኦሉኮያ ከሌጎስ ያጠናቀረዉን ዘገባ እንደሚከተለዉ ይደመጣል።
የናይጀርያ ገዥ ፓርቲ የፕሬዝዳት ጆናታንን አመራር በመቃወም፤ ሰባት ሀገረ-ገዢዎችና አንድ የቀድሞ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ፤ All Progressives Congress (APC በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ) ከተሰኘዉ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ ጋር የጋራ ፓርቲ የተመሰረተዉ ለወራቶች ከዘለቀ ከፍተኛ ቅራኔና ሽኩቻ በኋላ ነዉ። Alle Progressive Congress ፤ ከተለያዩ የመንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተጨማሪም ከታዋቂዎቹ ሁለት የናይጀርያ መንግሥት ተቀናቃኞች ፤ መካከል የወጣ ፓርቲ ነዉ። የመንግስት ተቀናቃኝ ፓርቲዎች በአንድ የተሰባሰቡበት በናይጀርያዉ ፖለቲካ ፓርቲ APC ፤ መርህም በመጭዉ ጎርጎረሳዊ 2015 ዓ,ም በሀገሪቱ በሚካሄደዉ ምርጫ ፕሪዚዳንት ጉድላክ ጆናታን፤ እንዳይሳተፉ ለማድረግ የተደረገ ሙከራ መሆኑም ግልፅ ነዉ። All Progressives Congress (APC ) ከተሰኘዉ የናይጀርያ መንግስት ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆኑት ቦሎ ቲኑቡ ፤ በምክር ቤት ይህ የተቃዉሞ ፓርቲ በአዲስ መልክ በመመሥረቱ ደስተኛ መሆናቸዉን ይናገራሉ፤
« በዚህ ክስተት ደስተኞች ነን። ሀገራችንን ከአንድ ቡድን ሥራ ለማስጣል እና የሚያስፈልጋትን ነገር ለሟሟላት በቁርጠኝነት ተነስተናል። »
በናይጀርያ የፖለቲካ ጉዞ የAPC ፓርቲ መመስረት ናይጀርያ ወደ ዲሞክራስያዊ ሥርዓት ከተቀየረች ከ 15 ዓመታት ወዲህ ትጠቀመዉ የነበረዉን ሁሉ ታጣለች። የዚህ ተፅኖ ደግሞ ፕሪዚዳንት ጆናታን ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን በጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ,ም ምርጫ ተሳታፊ አይሆኑም። የገዥዉ PDP ፓርቲ ብሄራዊ የፀጥታ ተጠሪ ፕሮፊሰር አደዋለ ኦላዲፖ እንደሚሉት ግን ሁኔታዉ ድንገተኛ ክስተት ቢሆንም፤ የፕሬዚዳንቱን የፖለቲካ ህይወት አያዉክም፤ «የፕሬዚዳንቱ የናይጀርያዉያኑን ፍላጎት የሚያሟሉ፤ ህዝቡ የሚፈልጋቸዉ አይነት ከሆነና በሳቸዉ እንዲመሩ የሚፈልግ ከሆነ፤ የዚህ ፓርቲ ቅንጅት የሳቸዉን የፖለቲካ እርምጃ የሚያስተጓጉል አይመስለኝም»
በናይጀርያዉ ፕሬዚደንት በጉድላክ ጆናታን እና በተቀናቃኞቻቸዉ መካከል ለመጭዉ የጎርጎረሳዊ 2015 ዓ,ም የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመቅረብ አለመቅረብ ክርክር እና ሽኩቻ የተጀመረዉ ከሁለት ዓመት በፊት በጎርጎረሳዉያኑ 2011 ዓ,ም ጉድላክ ጆናታን የፕሪዚዳንትነቱን በትረ ስልጣን ጨብጠዉ ቃለ ማኃላ እንደፈጸሙ ነዉ። እንደብዙዎች እምነት ሁሉ የሌጎስ ዩንቨርስቲ ተማሬዋ ናንሲ ሮበርትም፤ በናይጀርያ የሚገኙ ፖለቲከኞች በሀገሬቱ ከሚሰራዉ ሥራ ይልቅ በሀገሪቱ የሚመረጠዉ ፕሬዚዳንት ጉዳይ ያሳስባቸዋል፤ ይላሉ ፤ «በጎርጎረሳዊዉ 2015 ዓ,ም ማን ፕሬዚዳንት ሆኖ ይመረጣል በሚል የሚደረገዉ ፍክክር እና ትግል ለማድረግ ግዜዉ አሁን ገና ነዉ ። እንደኔ እምነት አንድ ፕሬዚዳንትን ለመምረጥ ከአሁኑ ከመጨቃጨቅ ፤ ሰዎች ተመርጠዉ እዲያገለገሉ የታዘዙበትን ስራ በመቀጠል ናይጀርያ ወደፊት እንድትራመድ ማድረግ አለቸዉ»
ዋንኞቹ የናይጀርያ ፖለቲከኞች የሀገሪቱን በሚሊዮኞች ዶላር የሞቆጠር ዓመታዊ የድፍድፍ ነዳጅ ሽያጭ ሰብሳቢዎች ናቸዉ። በከፍተኛ ሙስና የተዘፈቁት የናይጀርያ ዋንኞቹ የመንግስት ተጠሪዎች፤ በቀጣይ በከፍተኛ ፍጥነት አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ በሩጫ ላይ ይገኛሉ።

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Nigeria's Vice President Namadi Sambo (R) and Deputy President of the Senate Ike Ekweremadu stand for the national anthem during the national inter-denominational funeral rites of Nigeria's secessionist leader Odumegwu Ojukwu at Michael Opkara Square in Enugu, southeastern Nigeria, on March 1, 2012. Soldiers fired a 21-gun salute at the funeral of Odumegwu Ojukwu on Thursday as Nigerian leaders paid final respects to the man whose 1967 declaration of Biafran independence sparked a civil war. Forty-five years after he tried to split Nigeria asunder by proclaiming the Republic of Biafra, Ojukwu's coffin was draped in the national colours of white and green at the funeral service in the city of Enugu, attended by thousands. Ojukwu died in November in Britain at the age of 78 but his body was only flown back on Monday. AFP PHOTO/ PIUS UTOMI EKPEI (Photo credit should read PIUS UTOMI EKPEI/AFP/Getty Images)
ምስል AFP/Getty Images
Autor: unser Korrespondent in Abuja, Nigeria, Uwais Abubakar Idris über protestierende Menschen in Nigeria über Wahlfälschung Das Bild wude aufgenommen am 28.11.2013 in Abuja
ምስል DW/Uwais Abubakar Idris
Presidential candidate of the ruling Peoples Democratic Party and president elect Umar Yar'Adua (L) gives a press conference with his Vice-President Goodluck Jonathan in Abuja 23 April, 2007. Umaru Yar'Adua was declared winner of Nigeria's presidential election Monday, but foreign observers and opposition candidates slammed the credibility of a poll that cost at least 200 lives. AFP PHOTO PIUS UTOMI EKPEI (Photo credit should read PIUS UTOMI EKPEI/AFP/Getty Images)
ምስል Pius Utomi Ekpei/AFP/Getty Images