1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአሜሪካ የሶማሌያዉያን ክስ

ሰኞ፣ ነሐሴ 3 2002

የአሜሪካን መንግስት በግዛቱ እየኖሩ ሶማሊያ ዉስጥ አልሸባብ የተሰኘዉን ቡድን ለመደገፍ ተባብረዋል ባላቸዉ 14 ሶማሌያዉያን ላይ ክስ መሰረተ።

https://p.dw.com/p/Og0W
ምስል AP

በምኒያፖሊስ የሚኖሩ የሶማሌ አሜሪካዉያን ማኅበረሰብ በሽብር የተጠረጠሩ ዜጎች ላይ በተመሰረተዉ ክስ ከአሜሪካን የፌደራል የምርመራ ቢሮና ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እየሰሩ እንደሆነ ተገልጿል። ከሰማንያ ሺ በላይ ሶማሌያዉያን በሚኖሩበት በዚህ ግዛት ወጣቶች በአልሸባብ ቅስቀሳ እንዳይሸነፉ የሚሰራ አንድ ተቋም ስራ አስኪያጅ ቡድኑን ለመቀላቀል ልጆቻቸዉ ወደሶማሊያ የሄዱባቸዉ ወላጆች እጅግ ማዘናቸዉን ይናገራሉ።

አበበ ፈለቀ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ