1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአሸባሬነት የተጠረጠሩ ተከሳሾች ጉዳይ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 27 2001

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ከግንቦት ሰባት ድርጅት ጋር በመተባበርና በመደራጀት የተቀናጀ የሽብር ድርጊት ለመፈፀም በማሴር የተጠረጠሩት ተከሳሾች ፣ ክሳችንን ይከላከሉልናል ያሉትን የመከላከያ ምስክሮች ቃል ዛሬ አዳምጧል ።

https://p.dw.com/p/JNwK

ይኽው ችሎት ባለፈው ዓመት በቤንሻንጉል ጉሙዝና በኦሮምያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተነሳው ግጭት የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅመዋል ባላቸው ተከሳሾች ላይም ዛሬ ብይን አሳልፏል ። ታደሰ ዕንግዳው ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ታደሰ ዕንግዳው ሂሩት መለሰ