1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአካባቢ ተፈጥሮ የሚታዩ ለዉጦች

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 6 2006

በዓለማችን አንዳንድ አካባቢዎች ከዚህ ቀደም በዚያ ያልተለመደ ክስተት ሊታይ፤ ተክሎችም ሆኑ እንስሳትም ባልተለመዱበት ስፍራ የሚታዩበት ሁኔታ አለ።

https://p.dw.com/p/1Ct8b
Fotoreportage zur Problematik des Klimawandels in Bangladesch
ምስል DW/K.Hasan

ለዉጡ በሠዉ ሠራሽ እንቅስቃሴዎች ምክንያትም ሆነ ከአየር ንብረት ለዉጥ ጋ ተከትሎ የሚመጣ ሊሆን ይችላል። ይህን ማሳያ የሚሆን መልዕክት ከኢትዮጵያ ደርሶናል። እሱን መሠረት በማድረግ በአካባቢ ተፈጥሮ ላይ ተመራማሪ የሆኑትን ካናዳ ካልገሪ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙትን ዶክተር ጌታቸዉ አሰፋን በአየር ንብረት ለዉጥም ሆነ በሠዉ ሠራሽ እንስቃሴዎች በአካባቢ ተፈጥሮ ላይ ስለሚደርሱ ለዉጦች እንዲያስረዱን ጠይቀናቸዋል፤ ዶክተር ጌታቸዉ እነዚህን ለዉጦች በአካባቢና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከፋፍሎ ማየት እንደሚገባ በማሳሰብ በተለይ ከአየር ንብረት ለመወጥ ጋራ በቅርቡ የወጣ መረጃ ከጎርጎሪዮሳዊዉ 1900ዓ,ም ከነበረዉ ጋ በማነፃፀር የገጸ ምድር ሙቀት እንደሚጨምር የዛሬ ስድስትና ሰባት ዓመት የተነገረዉ እርግጠኛ መሆኑን ማሳየቱን ገልጸዋል። የአካባቢ ተፈጥሮ ላይ ለዉጦች እንዲከሰቱ ከሚያደርጉት መካከል ዶክተር ጌታቸዉ እንደሚሉት የሠዉ ሠራሽ እንቅስቃሴ አንዱ ነዉ። እንዴት ለሚለዉ ያስረዳሉ፤ ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ