1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአውሮፓ የኦሮሞ ተወላጆች ሰልፍ በብራሰልስ

ዓርብ፣ ሰኔ 13 2006

ኢትዮጵያ ውስጥ ፤ ከአዲስ አበባና አካባቢዋ ጋር የተጣመረውን የልማት መሪ አቅድ፤ የገጠር አርሶ አደሮችን ከርስት ጉልታቸው አፈናቅሎ ለችግር ይዳርጋል በማለት፣ በኦሮሚያ ፌደራል መስተዳድር የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ የዩንበርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ

https://p.dw.com/p/1CNBh
Straßburg Europäisches Parlament
ምስል picture-alliance/dpa

ባሳዩበት ወቅት ፣ ፖሊስ በወሰደው ርምጃ ፣ ተማሪዎች መገደላቸውን መቁሰላቸውንና ተይዘው መታሠራቸውን በመቃወም ፤ በጀርመን ሀገር የሚኖሩ የብሔሩ ተወላጆች በቅርቡ በርሊን ውስጥ አደባባይ በመውጣት የተቃውሞ ሰልፍ ማሳየታቸውን ከዚህ ቀደም መዘገባችን የሚታውስ ነው ። በዛሬው ዕለትም የአውሮፓው ሕብረትና የአውሮፓ ፓርላማ ፣ እንዲሂም የኔቶ መቀመጫ በሆነችው የቤልጅግ መዲና ብራሰልስ ከተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት በመሰባሰብ ዛሬ እኩለ ቀን ገደማ ላይ ተመሳሳይ ሰልፍ ማሳየታቸው ታውቋል። ሰ።ልፉ በተካሄደበት ሥፍራ ተገኝቶ የነበረው የብራሰልሱ ዘጋቢአችን ገበያው ንጉሤ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያው ንጉሤ

ተክሌ የኋላ

ኂሩት መለሰ