1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአዲስ አበባና በወልድያ የሙስሊሞች ተቃውሞ

ዓርብ፣ ሐምሌ 5 2005

በአዲስ አበባ አነዋር መስጊድ ለተወሰኑ ጊዜያት ጋብ ብሎ የነበረው የሙስሊሞች ተቃውሞ ዛሬ ቀጥሏል ። በወልድያም ተመሳሳይ ሠላማዊ ተቃውሞ ተካሂዷል ።

https://p.dw.com/p/1975C

በርካታ ሙስሊሞች በተገኙበት በአንዋር መስጊዱ ሠላማዊ ተቃውሞ ላይ ሙስሊሙ ከዚህ ቀደም ያቀረባቸው ጥያቄዎች እንዲመለሱና የታሰሩት የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ ጠይቋል ። በወልድያም ተመሳሳይ ሠላማዊ ተቃውሞ ተካሂዷል ። የአንዋር መስጊዱን ተቃውሞ የተከታተለውን የአዲስ አበባውን ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔርን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሪው ነበር ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ