1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአፍሪቃ ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች

ዓርብ፣ ሐምሌ 26 2005

በአፍሪቃ በህፃናት ላይ የሚካሄድ ወሲባዊ ንግድ እንዲገታ ህብረተሰቡና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ተጠየቁ ። በቅርቡ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደ ስብሰባ ላይ እንደተገለፀው በአፍሪቃ በሚሊዮች የሚቆጠሩ ወጣቶችና ህፃናት የወሲብ ንግድ ሰለባ ናቸው ።

https://p.dw.com/p/19J2M
ምስል picture-alliance/dpa

ችግሩን ለመቋቋም ፤ ቤተሰብ ህብረተሰቡ ትምህርት ቤቶች የየአካባቢው የአስተዳደር አካላት እንዲሁም መገናኛ ብዙሃን በጋራ ሃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው የስብሰባው ተካፋዮች አሳስበዋል ። ስብሰባውን ያዘጋጀው ዋና መስሪያ ቤቱ ታይላንድ የሚገኘው በህፃናት ላይ የሚካሄድ ወሲባዊ ንግድን ለማስቆም የሚንቀሳቀሰው ና በቅርቡ የኮንራድ ሂልተንን የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ያገኘው በምህፃሩ ኢክፓክት የተባለው ድርጅት ነው ። ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ