1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአፍጋሃኒስታን ጀርመን ወታደሮች ላይ የተጣለ ጥቃት

እሑድ፣ ሰኔ 12 2003

በሰሜናዊው አፍጋሃኒስታን ሰፍረው በሚገኙት የጀርመን ጸጥታ አስከባሪ ወታደሮች ላይ እንደገና የአጥፍቶ-ጠፊዎች የግድያ ሙከራ ተደረገ።

https://p.dw.com/p/RUUC
ምስል AP

የካቡል የአገርግዛት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በጥቃቱ ሳቢያ ቢያንስ ሁለት ሲቪሎች ሲገደሉ ሌሎች ዘጠኝ የሚሆኑም ቆስለዋል። ፖትስዳም ላይ ተቀማጭ የሆነው የተልዕኮው መምሪያ እንዳመለከተው በጀርመን ወታደሮች ላይ የደረሰ አንዳች ጉዳት የለም። አጥፍቶ-ጠፊው ግለሰብ በአውቶሞቢል ውስጥ ያጠመደውን ፈንጂ ያጋየው የጀርመን ወታደሮችን የጫነ የተሽከርካሪ አጀብ በአጠገቡ በማለፍ ላይ እንዳለ ነበር። ለጥቃቱ ታሌባኑ ዓማጺያን ሃላፊነቱን ሲወስዱ ይሄው አክራሪ ቡድን ባለፉት ሣምንታት የጀርመንን ወታደሮች ይበልጥ የጥቃት ዒላማ አድርጎ መቆየቱ ይታወቃል።

አዜብ ታደሰ
መስፍን መኮንን