1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአፍጋኒስታን የጀርመን ወታደሮች መገደልና ያስከተለዉ ስጋት

ሰኞ፣ ግንቦት 13 1999

ባለፈዉ ሳምንት በአፍጋኒስታን የተለያዩ ክልሎች አጥፍቶ ጠፊ ባነጎደዉ ቦንብ ከ 15 በላይ ሰዉ ህይወቱን አጥቶአል። በሰሜናዊው አፍጋሃኒስታን በደረሰዉ አንድ ከባድ የቦንብ ፍንዳታ ሶስት የጀርመን ወታደሮች፣ ስድስት የአፍጋኒስታን ሲቪሎች ሰለባ ሆነዋል። በአፍጋኒስታን እየተቀሰቀሰ ያለዉ የጥቃት ፍንዳታ አገሪቷን ለማቋቋም የተዘረጋዉን መረሃግብር እንዳይተጓጉል ያሰጋል

https://p.dw.com/p/E0c5
በኩንዱስ የጀርመን ወታደር
በኩንዱስ የጀርመን ወታደርምስል AP

የዶቼ ቬለዋ ሲቪለ ጎልተ በአፍጋኒስታን የጀርመን ወታደሮች ቢገደሉም ተልኮዋቸዉን ከመቀጠል ሌላ አማራጭ የላቸዉም! ስትል ሃታታ ጽፋለች
በአፍጋኒስታን እንደ አዲስ የተቀሰቀሰዉ ዉጥረት፣ በተለይም በአገሪቷ ሰፍረዉ በሚገኙት በጀርመን ወታደሮች ላይ የደረሰዉ ከባድ ጥቃት የምዕራቡ አለም ሁኔታን ጭጋጋማ ከማድረጉ ሌላ ፖለቲከኞችን እና የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቦአል። እስካሁን በአፍጋኒስታን በየትኛዉም ስፍራ ጸጥታዉ አስተማማኝ ክልል የለም! ጸጥታን ለመቆጣጠር አልተቻለም። ታሊባን-አማጺ ቡድን በወታደር መመከት አልተቻለም። በአፍጋኒስታን ባሉ በርካታ መስጊዶች ህዝብ ለቅዱስ ጦርነት እንዲነሳ ቅስቀሳ ይደረጋል። በፍልምያም ሆነ እንደ አጥፍቶ ጠፊ አንድ ታሊባን ከሞተ በምትኩ ሌላ አዲስ እና ታዳጊ ታሊባን ይከሰታል።
በአፍጋኒስታን የታሊባን አማጺ ቡድን መሪ ነዉ ተብሎ የሚጠረጠረዉ Mullah Dadullah ከአንድ ሳምንት በፊት በአሜሪካን ወታዶች ከተገደለ ወዲህ በአገሪቷ የጥቃት ፍንዳታ በመከሰት ጀምሮአል። Mullah Dadullah በአገሩ በአፍጋኒስታን ህዝብ በጭካኔዉ እና ሰዉ በማረዱ የታወቀ ወንበዴ ቢሆንም መገደሉ ከተሰማ ወዲህ በአገሪቷ የተለያዩ ክልሎች በድብቅ ለሃዘን የተቀመጠ አልጠፋም። የማጺዉ ቡድን መሪ መገደል ተከታዮቹን አድናቂዎቹን ለብቀላ ጋብዞአል።
በጀርመን ወታደሮች ላይ የደረሰዉ የሰሞኑ የብቀላ ፍንዳታ በጀርመን ከፍተኛ ስጋትን እና ጥርጣሪን ቀስቅሶአል። ቶርናዶ የተሰኘዉ የጀርመን የጦር አዉሮፕላን በአፍጋኒስታን ወታደራዊ ግዴታዎችን በሟሟላት ላይ ይገኛል። እዚህ ላይ ግልጽ በሆነ ቋንቋ ትላላች የዶቼ ቤለዋ Sibilly Golte፣ ቶርናዶ አዉሮፕላን በአፍጋኒስታን የተሊባን አማጺ ቡድን የት እንደሰፈረ ምን ያህል መሳርያ እንዳለዉ በምን እንቅስቃሴ ላይ እንዳለ ፎቶግራፍ በማንሳት ይቆጣጠራል። የዚህን የጀርመን ልዩ አዉሮፕላን ተግባር ደግሞ አማጺ ቡድኑ ታሊባን ጠንቅቆ ያዉቃል። ከሶስት ቀናት በፊት በሰሜናዊ አፍጋኒስታን በኩንዱስ ከደረሰ ፍንዳታ በኳላ በጀርመን፣ በአፍጋኒስታን ስላለዉ ልዩ አዉሮፕላን ተልኮ አዲስ ዉይይትን ቀስቅሶአል።

የወጣት ጀርመናዉያን ወታደሮች በአፍጋኒስን ኩንዱስ ላይ የጥቃት ፍንዳታ ሰለባ መሆን አስደንግጦአል። መሞትም አይገባቸዉም ነበር አሰኝቶአል። በአሁኑ ወቅት ምናልባትም በአፍጋኒስታን የጀርመን ወታደሮች መስፈር አጠያያቂ ሆንዋል። የጀርመን ወታደር በአፍጋኒስታን ሰሜናዊ ክልል ከሰፈረበት ግዜ ጀምሮ በመጀመርያ ደረጃ ህዝቡን በመርዳት በመንገድ በግንባታ በሆስፒታል ስራ በትምህርት ቤት ግንባታ በመሳሰሉ ቅድምያ ሉሰጡ በሚገባቸዉ ተግባሮች ላይ ተሰማርቶ ሲገኝ በመቀጠል ቶራናዶ የተሰኘዉን ልዩ አዉሮፕላን በማቅረብ የአሸባሪዎችን ጥቃት ለመከላከል ቁጥጥሩን ጀምሮአል።

በአፍጋኒስታን የወደፊት ሰላም መስፈን በአገሪቷ የተጀመረዉን መልሶ ግንባታ ስራ ያጠናክራል ሌላዉ አፍጋኒስታንን ለመርዳት የአለማቀፉ ማህበረሰብ በቦን የፒተርስበርግ የወጣዉ የመልሶ ግንባታ ዉጥን ገባራዊ ይሆናል። ይህ ሁሉ ሊሆን የሚችለዉ ግን የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ከሆነ ብቻ ነዉ። በዚህም ምክንያት በአፍጋኒስታን ተሰማርቶ የሚገኘዉ አለማቀፉ የእርዳታ እና የጸጥታ ሃይል ISAF በደቡባዊ የአገሪቷ ክፍል አስፈላጊነቱ አጠራጣሪ አይደለም።

በአፍጋኒስታን በመከሰት ላይ ያለዉ የአሁኑ ጥቃት በአገሪቷ ተሰማርቶ ያለዉን ወታደር እጥፍ የስራ ስትራቴጂ ወጥኖለታል። እስከዛሪም ቢሆን አንዱ የወታደር ሃይል ታሊባንን መመከት ሲሆን ሌላዉ አገሪቷን ለመደገፍ በተጀመረዉ የተለያየ የግንባታ ስራ መሰማራት ይሆናል። ይህን ሃታታ ጸሃፊ አገላላጽ በአፍጋኒስታን ያለዉ ወታደራዊ አገልግሎት መልኩን መቀየር አለበት ነዉ። በአንደኛ ደረጃ በአገሪታ ዉስጥ በሚደረገዉ የጸጥታ ቁጥጥር በርካታ ሲቢሎች ህይወታቸዉን አጥተዋል, በዚህም ምክንያት ህዝቡ በተሰማራዉ ወታደር ላይ እምነት በማጣት ላይ ነዉ። በሁለተኛ ደረጃ በአገሪቷ የሚደረገዉ የግንባታ ስራ ህዝቡ የመጀመርያ ተጠቃሚ መሆን አለበት።
ከዚህ ባሻገር ታሊባንን ማጥፋት በአፍኒስታን ህዝብ ድጋፍ ብቻ የተሳካ ይሆናል። ከላይ የተጠቀሱት በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ህዝቡ በአፍጋኒስታን ተሰማርቶ ከሚገኘዉ ከአለም አቀፉ የጸጥታ ሃይላት ጋር ተሳታፊ አልሆነም። ይህ ሁሉ ለዉጥ ማግኘት አለበት። አፍጋኒስታን በአማጽያኑ በታሊባን እጅ መልሳ መዉደቅ አይገባትም።
በምእራባዉያን የታቀደዉ ለኢራቅ መልሶ ግባታ ለኢራቅ ሰላም መንፈስ አለመሳካት ከኢራቅ ትንሽ ራቅ ብላ ለምትገኘዋ የአፍጋኒስታን እጣ እንዳይሆን ያሰጋል።