1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢራን እስር ላይ የቆዩ ሁለት ጀርመናዉያን ጋዜጠኞች ተለቀቁ

ቅዳሜ፣ የካቲት 12 2003

በቴህራን መንግሥት ኢራን ውስጥ ተይዘው የነበሩ ሁለት የጀርመን ጋዜጠኞች ከአራት ወራት እስር በኋላ መለቀቃቸዉን የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

https://p.dw.com/p/R2Ra
ምስል picture alliance/dpa
ሁለቱ የጋዜጠች ኢራን ቴብሪስ የጀርመን ኤንባሲ ሰራተኞች ጋር መሆናቸንዉም ተያይዞ ተገልጾአል። ሁለቱ “ቢልድ-አም-ሶንታግ” የተሰኘው የጀርመን ሣምንታዊ ጋዜጣ ዘጋቢዎች ኢራን ውስጥ ተይዘው የታሰሩት ባለፈው ጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ ነበር። ዘጋቢዎቹ የተወነጀሉት የሞት ቅጣት የተፈረደባትን የኢራናዊት ወንድ ልጅን እና ጠበቃዋን ቃለ መጠይቅ አድርጋችኋል በመባል ነዉ።