1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ድርጅት ተጠሪ መግለጫ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 28 2003

በምስራቅ አፍሪቃ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን ድርቅና ረሃብ በዘላቂነት ለመቋቋም የመሰረተ ልማት መስፋፋት ወሳኝ መሆኑን በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ድርጅት በምህፃሩ የ ተጠሪ አስታወቁ ።

https://p.dw.com/p/Re9y
ምስል dapd

አዲሱ የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተጠሪ አብዱ ድየንግ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከመሰረተ ልማት መስፋፋት በተጨማሪ ኃላ ቀር የግብርና ዘዴዎችን ማሻሻል እንደሚያሻም ተናግረዋል ። ለጋሾችም ሆኑ መንግሥታት ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስቀድመው ለሚያስተላልፏቸው የድርቅና የረሃብ ማስጠንቀቂያዎች ትኩረት ከመስጠት ይልቅ ረሃቡ ከተባባሰና የመገናኛ ብዙሀንን ሽፋን ሲያገኝ ብቻ መንቀሳቀሳቸው አንዱ ችግር መሆኑንም ጠቁመዋል ።

ጌታቸው ተድላ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ