1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር አረፉ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 6 2009

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሰደር ዮአኺም ሽሚድት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የአምባሳደሩ ዜና እረፍትየተሰማዉ በድንገት ነዉ። አምባሳደር ዮአኺም ሀገራቸዉ ጀርመንን ወክለዉ ወደ ኢትዮጵያ በአምባሳደርነት ተሾመዉ የሄዱት በጎርጎረሳዊ 2014 ዓ.ም ሐምሌ ወር ነበር።

https://p.dw.com/p/2ebIz
Äthiopien Joachim Schmidt
ምስል Deutsche Botschaft Äthiopien

አምባሳደር ዩአኺም በኢትዮጵያ እጅግ ተወዳጅ እና ታዋቂ እንዲሁም ከማኅበረሰቡ ጋር እጅግ ቅርበት አላቸዉ ከሚባሉ የዉጭ ሃገራት አምባሳደሮች ቀዳሚዉን ስፋራ ይዘዉ እንደሚገኙ ይነገራል። በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ወጣቶችን በማሰባሰብ በስፖርት በተለይም በእግር ኳስ ጨዋታ እንዲሁም የጀርመንን ታሪክ በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ነበሩ። 

አምባሳደር ዮአኺም ተሹመዉ ወደ ኢትዮጵያ ከመሄዳቸዉ በፊት በቦስኒያ ሄርዞጎቪና እንዲሁም ከዚያ ቀደም ሲል በሰርቢያ በአምባሳደርነት ሀገራቸዉን አገልግለዋል። አምባሳደር ዮአኺም ሽሚድት በአፍሪቃ ኅብረት የጀርመን አምባሳደርም ነበሩ። ከዚህም ሌላ በጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒሥቴር በአምባሳደርነት ማዕረግ የዉጭ ንግኙነት አገልግሎት አካዳሚ ኃላፊም ሆነዉ ማገልገላቸዉን በአዲስ አበባ የጀርመን ኤምባሲ ያወጣዉ መግለጫ ያመለክታል። 

Äthiopien Joachim Schmidt
ምስል Deutsche Botschaft Äthiopien

በአምባሳደር ዮአኺም ሽሚድትን ሞት ምክንያትም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የሚገኘዉ የጀርመን ኤምባሲ ከሰኔ 7 እስከ 9 ከቀኑ 4 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ተኩል ድረስ ፤ በሀገሪቱ የሚገኙ የማኅበረሰብ አካላትና የመንግሥት ባለስልጣናት በሃዘን መግለጫ ደብተር ላይ የሃዘናቸዉን መግለፅ የሚችሉበትን መረሐ-ግብር ይፋ ማድረጉን ገልጿል። 

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ