1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የፖለቲካ መቻቻል እንዴት?

እሑድ፣ የካቲት 26 2009

የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ እና ሃገር ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ 21 ፓርቲዎች አዲስ ድርድር ጀምረዋል። ድርድሩ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ቀዉስ በሰላም ለመፍታት ጥሩ አማራጭ እንደሆነ ብዙ የፖለቲካ ታዛቢዎች ይናገራሉ። ዉጤቱ አግባቢ መሆኑን ግን ብዙዎች በጥርጣሪ ነዉ የሚያዩት።

https://p.dw.com/p/2Yf3m
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

በኢትዮጵያ የፖለቲካ መቻቻል እንዴት?

ለጥርጣሪያቸዉ ከሚሰጥዋቸዉ ምክንያቶች አንዳንዶቹ ሁሉም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዉጭ የሚገኙት ጭምር አለመሳተፋቸዉ፤ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ሌሎች ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች እስር ቤት እያሉ ድርድር መጀመሩ፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ልዩነታቸዉን አቻችለዉ ችግራቸዉን በዉይይት የመፍታት ባህል አለመታወቁ የሚሉት ይገኙበታል። የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በተለያዩ ጊዜያት የዉይይትና የድርድርን አስፈላጊነት ይናገራሉ። በብዙዎች አስተያየት አንዱ ሌላዉን ለማጥፋት ከማድባት በስተቀር አንዱ ከሌላዉ ጋር በጠረቤዛ ዙርያ ተወያይቶ ወይም ተደራድሮ ችግሮቹን ለማስወገድ ሲሞክር አይታይም ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ፖለቲከኞች በ 21ኛዉ ክፍለ ዘመን ከመወያየትና ከመደራደር ይልቅ መናቆርና መጋጨቱን እንደቀጠሉበት ነዉ። ችግሩ ምንድን ነዉ? ለሚለዉ ትክክለኛ መልስ ማግኘትም ቢሆን ከባድ ነዉ። የተለያዩ ምሁራን እና ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ ግን  የዴሞክራስያዊ ባህል አለመታወቅ አስተሳሰብን በሌላ ላይ በኃይል የመጫን ፍላጎት ጠንካራ መሆን፤ ተቃዋሚን እንደጠላት የመመልከት እምነት መኖሩን በተደጋጋሚ ይጠቅሳሉ። ይህ የማይጠቅም የፖለቲካ አለመቻቻልና አለመግባባት ስር የሰደደ ነዉ። ስር የሰደደዉን በፖለቲካ አለመቻቻልና አለመግባባት እንዴት ማስወገድ ይቻላል? በኢትዮጵያ የፖለቲካ መቻቻል እንዴት? በሚል ርዕስ የተወያዩልን፤ ፕሮፊሰር ብርሃኑ መንግስቱ በዩናይትድ ስቴስትስ ኦልድ ዶሚኒየን ዮንቨርስቲ መምህርና የግጭትና መንስኤ ላይ የተለያዩ ምርመራዎችን በማድረግ ግጭት አፈታትና እርቅ ላይ ስልጠናን በመስጠት ላይ የሚገኙ፤ የዉይይት መጽሔት ዋና አርታዒ ጠበቃ ሞላ ዘገየ፤ እንዲሁም በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚሳተፉት፤በሰዋሰዉ ብርኃን ቅዱስ ጳዉሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአዲስ ኪዳን መምህር መጋቤ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ ናቸዉ።  ሙሉ ዉይይቱን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ