1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢንዱስትሪዉ ምትክ የባህል ተቋማት ግንባታ

እሑድ፣ ጥር 2 2002

በዝነዉ የአዉሮጻዉያን አዲስ አመት በጀርመን ትልቅ ግዛት እንደሆነ በሚታወቀዉ እዚህ በኖርዝ ራይን ዊስት ፋልያ ግዛት በሚገኘዉ የሩር አካባቢ የአዉሮጻ የባህል ማዕከል በመሆን ተመርጦአል።

https://p.dw.com/p/LPZi
ምስል picture alliance/dpa

የፈራረሱ ኢንዱስትሪዎችንና ቀድሞ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ፍብሪካዎችን በማፈራረስ ለምና መስብ የተሞላዉ መንደር ለማድረግ ስራዉ ተጀምሮአል። አካባቢዉ በሚገኘዉ የሩር ወንዝን ስያሜ ይዞ ያለዉ አካባቢ 5 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርበት ሲሆን በጀርመን ዉስጥ ካሉ አካባቢዎች ሁሉ በርካታ ህዝብን አቅፎ በመያዙ አንደኛ ከአዉሮጻ አገሮች ደግሞ ሶስተኛ ነዉ። የሩር አካባቢ በርካታ ኢንዱስትሪን አቅፎ የያዘ በተለይም የድንጋይ ከሰል የሚወጣበት አካባቢ በመሆኑ ነበር፣ በርካታ ነዋሪዎች በአካባቢዉ ሰፍረዉ የሚገኙት። የከሰል ድንጋይ ተፈላጊነቱ እየቀነሰ ሲሄድ በዛዉ አካባቢ ያሉ ህዝቦች አካባቢያቸዉን በመቀየር በፋብሪካዉ ምትክ የጸሃይ ወይም የነፋስ ሃይል ምንጭ መሰብሰብያ በመትከል የመሪቱን ለምነት በመጠበቅ ቦታዉ ልዩ መስብ እንዲህን አድርገዉታል። በዶትሙንድ በሚገኘዉ የኢኮነሚ እድገት ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ፓስካል ሌዱኔ ስለ አካባቢዉ እድገት «ይህ ቦታ ብቻዉን ሳይሆን ከዚህ በምዕራብ በኩል ያለዉን ቦታ ይዞ 3 ኪሎ ሜትር ዘልቆ ያለዉን ቦታ በመጨመር ነዉ እድገት ያሳየዉ። አንድ በቴክኖሎጂ የተራቀቀ ፓርክ አለዉ፣ እንደገና የቴክሎጂ ማእከልም የሚባል ክፍልን ሁሉ አካቶአል። ቦታዉ የመኖርያ ሞታንም አጠቃልዋል»
በ 1950 ዎቹ በጀርመን የታየዉን ከፍተኛ የኢኮነሚ እድገት መሰረት የሆነዉ ይኸዉ የሩር አካባቢ በጀርመንኛ መጠርያዉ Ruhrgebiet የነበረዉን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ የሚያመርተዉ ምርት በአለም ገበያ ፈለጊነቱ እየቀነሰ በመምጣቱ ይህንን ግዙፍ እንዱስትሪ ለማፍረስ የአመታት ግዜን ጠይቆበታል።
በዶርትሙንድ ከተማ አቅራብያ 30 የእግር ኻስ መጫወቻ ቦታን የሚያህል ክልል ላይ በቀድሞ የከሰል ድንጋይ ማዉጫ የነበረዉ ቦታ ከአዉሮጻዉያኑ 2001 አ.ም ጀምሮ ታጥሮ ምንም ሳይሰራበት የቆመ ቦታ ነበር። በአሁኑ ወቅት ግን በዚህ ትልቅ ክልል ላይ ሸለቆ ቦታዎችን በመድፈን እና በማስተካከል ሰዉ ሰራሽ ባህር እና በዉሃ በመታገዝ የተለያዩ መስዕቦችን እና መዝናኛዎችን ለመስራት የሚደረገዉ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ስራዉ ተጀምሮአል። «Ruhrgebiet የተሰኘዉ በዚህ በኖርዝ ራይን ዊስት ፋልያ ግዛት የሚገኘዉ ትልቁ አካባቢ ለየት የሚያደርገዉ ቀደም ሲል ቦታዉ ሙሉ በመሉ የኢንዱስትሪ አካባቢ በመሆኑ ነበር። የብረታ ብረት ክምር፣ የሃይል ምንጭ፣ አልያም የተለያዩ ማዕድናት ቁልል ነበር የሚታየዉ። በሌላ በኩል የሚደንቀዉ ደግሞ የስራ አጥ ቁጥርም ከፍተኛ ነዉ»
የአዉሮጻዉ ህብረት ሸንጎ፣ ከአዉሮጻዉያኑ 1985 ጀምሮ ቢያንስ አንድ ከተማ የአመቱ የአዉሮጻ የባህል ከተማ በማለት ስያሜ መስጠት የጀመረዉ። በኖርዝ ራይን ዊስፋልያ ግዛት ዉስጥ ታላላቅ ኢንዱስትሪ ፋብሪካ የሚገኝበት ትልቁ የሩር አካባቢ ማለት በ Ruhrgebiet የሚገኘዉን የኤሰን ከተማ ደግሞ የባህል ማእከሉ ዋና ከተማ ብሎ ተሰይሞአል። Ruhrgebiet ተብየሎ የሚታወቀዉ የሩር አካባቢ ያካተተዉ 35 ከተሞችን ሲሆን ቀድሞ ይንቀሳቀስ የነበረዉን ፋብሪካ እና ኢንዱስትሪ ክልል በማጽዳት ከተለያዩ የአለም አገራት የሚመጡ ጉብኝዎችን ለመሳብ እና ለማስደሰት 300 ፕሮጄዎችን በማቋቋም በአመቱ ዉስጥ 2500 ያህል የተለያዩ ዝግጅቶችን ለተመልካች ክፍት እንደሚያደርግ ተጠቅሶአል።

BdT Menschen fahren Schlittschuh auf einer Eisflaeche in der Kokerei Zollverein in Essen
የቀድሞ ኢንዱስትሪ መንደርን ዘንድሮ ደግሞ ህዝቦች የበረዶ መንሸራተቻ መዝናኛ አድርገዉታል።ምስል AP

አዜብ ታደሰ