በእስራት ያሉት የበቀለ ገርባና የጓደኞቻቸው የረሃብ አድማ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 19 2008ማስታወቂያ
አቃቤ ሕግ 22ቱ ታሳሪዎች ላይ ክስ ሲመሰርት የአገሪቱን የፀረ-ሽብር ሕግ ተጠቅሞ ሲሆን፣ ተከሰሾቹ ግን ክሱን ውድቅ በማድረግ እየተከራከሩ መሆናቸውን ጠበቃቸው አቶ ኢብሳ ከተወነጀሉበት ክስ ነፃ መሆናቸዉ ከችሎት የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ከዚያም አልፎ የእስረኞችን አያያዝ እና ወህኒ ቤት ዉስጥ የሚደርስባቸዉ የተለያዩ በደሎችን በተመለከተ አቶ በቀለ ገርባ እና ሌሎች የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ኮሚቴ እስረኞች፣ ችግራቸዉ እንዲሰማላቸዉ ታስረዉ ባሉበት ማረምያ ቤት ላለፉት ስድስት ቀናት የረኃብ አድማ ላይ መሆናቸዉን የገለፁት የፓርትዉ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ገብሩ ገብረማርያም ፤ ከረሃቡ አድማ በኋላ የሆነዉን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።
የእስረኞቹ ጠበቃ አቶ ወንድሙ ኢብሳ እስረኞቹ የረኃብ አድማ የመቱበትን ምክንያቶች የእስር ቤት ዉስጥ ያለዉን የኢስረኞች አያያዝ እንድሁም አሁን አገርቱ ዉስጥ ያለዉን ተቃዉሞ አስመልኪቶ መሆኑን ይናገራሉ።
የረሀብ አድማ የመቱት እስረኞች ላይ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ አንድ መፍትሔ ሊሰጥ ይገባል ስሉ ጠበቃ አቶ ወንድሙ ጠቅሰዋል።
ለበለጠ መረጃ አዉዲዮን ያዳምጡ
መርጋ ዮናስ
አረያም ተክሌ