1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኦሮሚያ ተቃውሞ ቢያንስ 75 ሰዎች ተገድለዋል

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 9 2008

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሒውማን ራይትስ ዎች ትናንት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰውና ሣምንታትን ባስቆጠረው ተቃውሞ ቢያንስ 75 ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/1HQWT
Human Rights Watch Logo

ከአዲስ አበባ 80 .. ርቀት ላይ በምትገኘው ጊንጪ ከተማ ተጀምሮ ወደ መላ ኦሮሚያ ለተስፋፋው ተቃውሞ የኢትዮጵያ መንግስት በሰጠው ምላሽ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የተናገሩት የድርጅቱ የአፍሪቃ ክፍል ምክትል ኃላፊ ሌስሊ ሌፍኮው የከፋ ደም መፋሰስ ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በከተሞችና ከፍተኛ የትምርት ተቋማት የተዛመተው እና የአዲስ አበባ ከተማን ከአጎራባች አካባቢዎች ጋር ለማስተሳሰር የታቀደው ማስተር ፕላን ላይ በተነሳው ተቃውሞ የሞቱት ሰዎች ቁጥር አምስት ብቻ መሆናቸውን አስታውቋል።

Berlin Demonstration von Oromo-Aktivisten
ምስል DW/H. Kiesel

የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ከመሬት መነቀልን ጨምሮ ለአመታት የተከማቸ ቅሬታ፤ የዴሞክራሲ እጦት፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና አስከፊ ድህነት ለተቃውሞው ተጨማሪ ገፊ ምክንያቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሌስሊ ሌፍኮው የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን «ሽብርተኛ» ሲል መፈረጁ እና ተቃውሞው በተስፋፋባቸው አካባቢዎች የጦር ኃይል ማሰማራቱ ሁኔታውን ሊያባብስ የሚችል አደገኛ ውሳኔ ሲሉ ወቅሰዋል።

እሸቴ በቀለ

ማንተጋፍቶት ስለሺ