1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኦሮምያ ክልል የቀጠለዉ ተቃዉሞ

ዓርብ፣ የካቲት 11 2008

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን የተቀሰቀሰዉና የሰዉ ሕይወት የጠፋበት ግጭት አሁንም አለመብረዱ እየተነገረ ነዉ። አንድ የአካባቢዉ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ በስልክ እንደገለጹት የፊደራል ፖሊሶች ሰርገኞች ላይ ተኩስ ካስነሱ በኋላ ዉጥረቱ አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ እየተዛመተ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1HypK
Karte Ethiopia und Eritrea ENG

[No title]

የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸዉ አካባቢዉ ላይ በሚገኝ ማሳ፤ የእምነት ተቋማትና ደን፤ እንዲሁም የመንግሥት መሥርያ ቤት ላይ ጥቃት የጣሉት ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር ቢገኙም መንግሥት ከአካባቢዉ ነዋሪ ጋር በመተባበር ያልተያዙትን በህግ ከለላ ዉስጥ ለማስገባት ክትትሉን እንደቀጠለ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የዩናይትድ ሰቴትስ፣ የእንግሊዝና የኖርዌይ መንግሥታት ዜጎቻቸዉ ወደ ኦሮምያ የሚጓዙ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በዚህ ሳምንት ማሳሰባቸዉ ይታወቃል። አንድ የምዕራብ አርሲ ዞን ነዋሪንና፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚንስትር አቶ ጌታቸዉ ረዳን አነጋግረን ዘገባ አጠናቅነራል።

ከለፈዉ ሳምንት ጀምሮ በምዕራብ አርሲ ዞን የተቀሰቀሰው ግጭት በተለይ ሻላ፣ ሲራሮና ሻሸመኔ ወረዳዎች ውስጥ መስፋፋቱን፤ የነገሩን የአካባቢዉ ነዋሪ አቶ በቀለ ኃይሌ የግጭቱ መነሻ እሁድ አርሲ ውስጥ አጄ አካባቢ እንደነበር ነዉ የገለፁት።

ሰኞ የካቲት 7 ቀን በምዕራብ አርሲ ሲራሮና ሻላ በተባሉ አካባቢዎች የሰባት የፀጥታ ኃይላት ሕይወት የጠፋበትና ንብረት የወደመበት ግጭትን ካስነሱት ታጣቂዎች የተወሰኑት መያዛቸዉና አካባቢዉ ላይ የተነሳዉ ንብረት የማዉደም እንቅስቃሴም ከሞላ ጎደል በቁጥጥር ስር እየዋለ መሆኑን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ገልፀዉልናል።

የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ እንደገለፁት የአካባቢዉ ነዋሪ ከመንግሥት ጋር በመሆን ለሰላም መስፈን ጥረት እያደረገ ነዉ። ሙሉዉን ቃለ ምልልስ የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ