1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኦሮምያ ዩኒቨርስቲዎች የተቋረጠው ትምህርትና የታሰሩ ተማሪዎች

ረቡዕ፣ ግንቦት 6 2006

በኦሮምያ ክልሎች ለአዲስ አበባና ለኦሮምያ ልዩ ዞን በመዘጋጀት ላይ ያለውን የተቀናጀ ማስተር ፕላን በመቃወም አመፅ ከተነሳ ወዲህ በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች ተቋርጦ የነበረው ትምህርት እንደሚጀምር ተገልጿል ። በአንዳንድ አካባቢዎችም የታሰሩ ተማሪዎች ተለቀዋል ።

https://p.dw.com/p/1Bzk7
Addis Abeba
ምስል picture alliance / landov

በተለይ በኦሮምያ ክልል በጉጂ ዞን በነገሌ ቦረና ከተማ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ከታሰሩት መካከል አብዛኛዎቹ ተለቀው 2ቱ እስካሁን እንዳልተፈቱ ነዋሪዎች ሲናገሩ ፖሊስ ግን የታሰሩት በሙሉ ተለቀዋል ይላል ። አንድ የከተማዋ ነዋሪ ሰዎቹ እንዴት እንደተያዙ ለዶቼቬለ ገልፀዋል ።የተያዙትም በከተማዋ የሚገኝ የነርሶች ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና አንዳንድ የከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን የገለፁት እኚሁ ነዋሪ ባላቸው መረጃ መሰረት እስከ ትናንት ድረስ ሁለት አልተለቀቁም።የነገሌ ቦረና ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊ ኢንስፔክትር ኤዶም ዱባ እንደተናገሩት ደግሞ የተያዙት ሰዎች ቁጥር 48 አይደለም ። የታሰሩት በሙሉም ተለቀዋል ።በሌላ በኩል በኦሮምያ ክልል በአመፅ ምክንያት ትምህርት አቋርጠው ከነበሩ የዩኒቨርስቲዎች ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት መደረጉን የኦሮምያ ምክር ቤት አስታውቋል ። ተማሪዎቹ የተቃወሙት በአአ ዙሪያ የሚገኙትን ሱሉልታ ቡራዩ መናገሻ ና የመሳሰሉትን ከተሞች ያካተተውን የአዲስ አበባና የኦሮምያ ሉዩ ዞኖች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ነው የጨፌ ኦሮምያ ምክር ቤት የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ደክሲሶ ሁሴን በተለይ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ትምህርት ለመጀመር የሚያስችሉ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን ተናግረዋል ።አቶ ደክሲሶ ትምህርት መጀመሩን ግን አላረጋገጡም ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ