1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኦንግ ሳን ሱ ቺ ላይ የተላለፈው ብይን

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 5 2001

በማይናማር በዋነኛዋ የመንግስት ተቃዋሚ፡ ብሄራዊ ዴሞክራቲክ ሊግ ፓርቲ መሪ ኦንግ ሳን ሱቺ ላይ አንድ

https://p.dw.com/p/J7o2
ምስል AP

የሀገሪቱ ፍርድ ቤት በይኖት የነበረውን የሶስት ዓመት እስራት ከጉልበት ስራ ጋር ቅጣትን የሀገሪቱ ወታደራዊ መሪ ጀነራል ታንሹዊ ዛሬ ወደአስራ ስምንት ወራት እስራት ቀየሩት። ኦንግ ሳን ሱ ቺ በቁም እስር እያሉ ህግ በመጣስ አንድ አሜሪካዊ በዋና ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲገባ ፈቅደዋል በሚል ነበር ክስ የተመሰረተባቸው። ካለፉት አስራ አራት ዓመት ወዲህ በቁም እስር የሚገኙት የኖቤል ሰላም ተሸላሚዋ ኦንግ ሳን ሱ ቺ ላይ የተላለፈው ብይን ዓለም አቀፍ ወቀሳ አፈራርቆዋል፤ የአውሮጳ ህብረትም በዚችው ሀገር ላይ ያሳረፈውን ማዕቀብ እንደሚያጠናክር አስታውቋል።

ይልማ ሀይለሚካኤል/አርያም ተክሌ/ሸዋዬ ለገሠ