1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኬንያ የሦስት ቀን ሐዘን ታወጀ

እሑድ፣ መጋቢት 27 2007

በኬንያ ጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ አልሸባብ የተሰኘው የሶማሊያው እስልምና አክራሪ ታጣቂ ቡድን ባደረሰው ጭፍጨፋ ላለቁት 150 ግድም ሰዎች ኬንያ የሦስት ቀን ብሔራዊ ሐዘን አወጀች።

https://p.dw.com/p/1F30Q
Kenia Garissa Universität Anschlag Kenias Präsident Uhuru Kenyatta äußert sich zu demAnschlag
ምስል picture-alliance/dpa/ZUMA Press

በጎርጎሪዮሳዊው አቆጣጠር መሠረት ዛሬ በሚከበረው የፋሲካ በዓል ኬንያ ውስጥ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ አብያተ ክርስቲያናት ሐሙስ ዕለት በታጣቂዎች የተገደሉትን ሰዎች ለማሰብ በሚል ባንዲራዎቻቸውን ዝቅ አድርገው ማውለብለባቸው ተዘግቧል። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ «በተቻለ መጠን እጅግ በከፋ መልኩ» የበቀል ርምጃ እንወስዳለን ሲሉ ዝተዋል። በኬንያ ብሔራዊ ኅብረት እንዲኖርም መጠየቃቸው ተዘግቧል። ኬንያ ጦሯን ከሶማሊያ እስካላስወጣች ድረስ «የተራዘመ አሰቃቂ ጦርነት» ማኪያሄዳችን «በደም መታጠብ መቀጠሉ» አይቀርም ሲል አልሸባብ ዝቷል። አልሸባብ ዛቻውን ከሰነዘረ ከሠዓታት በኋላ ጋሪሳ ውስጥ የሚገኙ ፖሊሶች ዩኒቨርሲቲው ውስጥ የተገደሉትን አራቱን የአልሸባብ ታጣቂዎች አስክሬን በክፍት ፒክ አፕ መኪና ጭነው በበርካታ ሰዎች ታጅበው ሲንቀሳቀሱ መታየታቸውም ተዘግቧል። ከተገደሉት ታጣቂዎች መካከል አንደኛው ኬኒያዊ ሶማሌ መሆኑን እንዲሁም በሕግ ትምኅርት መመረቁንም የኬንያ ፖሊስ ይፋ አድርጓል። ከሐሙሱ ጥቃት የተረፉት 600 የጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ዩኒቨርሲቲውን ለቀው ወደ የመጡበት ቦታ መሄዳቸውም ተጠቅሷል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ