«በወጣትነት ያባከንኳት ጊዜ»- አቤሰሎም አርዓያ
ቅዳሜ፣ ግንቦት 9 2006አቤሰሎም አርዓያ ይባላል። ዛሬ ወጣት አይደለም። የወጣትነት ጊዜውን ግን በደንብ ያስታውሳል። በወጣትነቱ ስላባከነው እና ከመንገድ ስለወጣበት ጊዜ ገልፆልናል።
ጭንቀት ወይም ስራ ማጣት ወጣቶች ሱሰኛ ከሚሆኑባቸው ምክንያቶች ጥቂቶቹ ናቸው። ከዛ ደግሞ በራስ አነሳሽነት? ወይስ በሌሎች ሰዎች ግፊት? የሚለው ጥያቄም አለ፤ የአቤሰሎምምክንያቱ ሁለቱም ነበር። አቤሰሎምእንደቀልድ የጀመረው ሱስ ሆኖ ከዕለት ከዕለት ህይወቱ መለየት የማይታሰብ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። ምንም እንኳን አደባባይ ተቀምጦ ጫት ባይቅምና ሲጋራ ባያጨስም፤ በወቅቱ ሱሰኛነቱ የሚያውቁ ፤እንዲተውም የመከሩትም አልጠፉም።አቤሰሎምእድለኛ ነው። ከገባበት ሱስ ራሱ ባኖ ለመውጣት ብዙ ጊዜ አልፈጀበትም። የገጠመው ከፍተኛ ሀዘን ከሱሱ አላቆታል።
አቤሰሎም ከመጠጥ፣ ሲጋራ እና ጫት ያለፈ ሌሎች አደንዛዥ እፆች እንዳልወሰደ ገልፆልናል። ቢሆንም እስከመቼ እንደዚህ እቀጥላለሁ ሲል ራሱን የጠየቀው አቤሰሎም ሁሉን ነገር ርግፍ አድርጎ ለመተው ቢወስንም፤ መጀመሪያ ላይ ከብዶት ነበር።ዛሬ አቤሰሎም ተቀይሯል።በእድሜም ከጎልማሶቹ ይቆጠራል። « አርባን ማየት ጀምሬያለሁ» ይላል። ዛሬ በፊልም ስራ የተሰማራው አቤሰሎም አርዓያ ፤በወጣትነት በሱስ ስላባከነው ጊዜ አጫውቶናል።
ለበለጠ የድምጽ ዘገባውን ከፍተው ዝግጅቱን ይስሙ።
ልደት አበበ
ነጋሽ መሀመድ