1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ዜጎች ሳምንት

ረቡዕ፣ ጥቅምት 3 2008

ከአፍሪቃ አርአያ ከሆኑና ለወገኖቻቸው ውጤታማ ሥራ በመሥራት በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት መካከል የቤኒኗ ተወላጅ የግራሚ ተሸላሚዋ ድምፃዊት አንጀሊክ ኪጆ ለዝግጅቱ ታዳሚዎች ልምድዋን አካፍላለች።

https://p.dw.com/p/1GoTc
USA John Kerry Außenminister
ምስል Getty Images/M. Wilson


ዓለም ዓቀፍ በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ዜጎች ሳምንት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው ። ሳምንቱን ምክንያት በማድረግ ባለፈው አርብ በአሜሪካን ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአንድ ቀን ዝግጅት ተኪሂዶ ነበር። በዝግጅቱ ላይም የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። ታዋቂና በአርአያነታቸው የሚጠቀሱ የውጭ ዜጎች በተገኙበት በዚሁ ዝግጅት ላይ የውጭ ዜጋ የተሰደደበትን ሃገርም ሆነ የትውልድ ሃገሩን ለመርዳት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተገልጿል ።ወደ ሃገሩ በሚልከው ገንዘብም ሃገሩን እንደሚጠቅም ተወስቷል። ከአፍሪቃ አርአያ ከሆኑና ለወገኖቻቸው ውጤታማ ሥራ በመሥራት በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት መካከል የቤኒኗ ተወላጅ የግራሚ ተሸላሚዋ ድምፃዊት አንጀሊክ ኪጆ ለዝግጅቱ ታዳሚዎች ልምድዋን አካፍላለች። ባለፈው ሰኞ መታሰብ የጀመረው የዳያስፖራ ሳምንት እስከ ፊታችን ቅዳሜ ይዘልቃል ።

መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ