1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዓለም የጦር ወንጀለኛ ፍርድ ቤት እና የአፍሪቃዉያን አመለካከት

ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 5 2005

የኬንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ፣ በ 2000 ዓ ም፤ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ፍርድ ቤት በቆረጠው ቀጠሮ ዛሪ ደን ኻኽ ኔደርላንድ በሚገኝበት ፍርድ ቤት ቀረቡ። በኬንያ 2000 ዓ ም በነበረዉ ምርጫ ማግሥት ለሳምንታት በተካሄደው የጎሣዎች ግጭት

https://p.dw.com/p/19fa8
ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ፍርድ ቤት

ከ 1,000 በላይ ኬንያውያን መገደላቸውና ከ 600,000 በላይ ህዝብ ከቀየው መፈናቀሉን ተከትሎ፤ የዓለም ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ፍርድ ቤት፤ ፕሬዚዳንት ዑሑሩ ኬንያ እና ምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በተፈጠረው ሁከትና ግድያን አቀነባብረዉ፤ በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ሲል ክስ ማቅረቡ ይታወቃል። ከዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ፍርድ ቤት የመዉጣት ዉሳኔን የኬንያ መንግስት ብቻ ማፅደቅ ቢችልም ቅሉ ባሳለፍነዉ ሳምንት የኬንያዉ ምክር ቤት ሀገሪቱ ከ ICC እንድትወጣ በውሳኔ ከደገፈ በኋላ፤ የICC አባል ሀገር የሆነችዉ ዩጋንዳ፤ የኬንያን ምክር ቤት ዉሳኔ አወድሳለች። ይህ የዩጋንዳ አቋም ምንን ያመለክታል፤ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህር የሆኑት የህግ ባለሞያዉ ዶክተር ያዕቆብ ኃይለማርያ ይመልሱልናል፤

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ