1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመን እና ውጊያው

ሰኞ፣ ጥር 15 2009

በየመን ፕሬዚደንት አብድ ራቦ ማንሱር ታማኝ ጦር እና በሁቲ ዓማፅያን  መካከል በተካሄደው ውጊያ የብዙዎች ሕይወት ጠፋ።  የፀጥታ ኃይላት እና የነፍስ አድን ሰራተኞች ትናንት እንዳስታወቁት፣ ተፋላሚዎቹ የሞካ ግዛት ለመያዝ ካለፈው ቅዳሜ ወዲህ በጀመሩት ውጊያ ቢያንስ 45 የሁቲ ዓማፅያን እና ከአስር የማያንሱ የመንግሥት ታማኝ ወታደሮች ተገድለዋል።

https://p.dw.com/p/2WG7i
Jemen Huthi Rebellen
ምስል Reuters/K. Abdullah

mmt Q & A(Jemen _ Lage nach heftigen Gefechten) - MP3-Stereo


አንዳንድ የውጭ ዜና ምንጮች የየመን መንግሥት ጦር  በቀይ ባህር ጠረፍ የሚገኘውን የሞካን ግዛት ከዓማፅያኑ እንዳስለቀቀ ሲዘግቡ ተሰምቷል። የመንግሥቱ ጦር ከሁለት ሳምንታት በፊት በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ መካከል የሚገኘውን ስልታዊውን የባብ ኤል መንደብ መተላለፊያ መልሶ በተቆጣጠረበት ጊዜ ነበር የሁቲ ዓማፃያን ወደ ሞካ ግዛት ያፈገፈጉት።
 የመን ውስጥ ከመስከረም 2014 ዓም ወዲህ የርስበርስ ጦርነት እንደቀጠለ ነው። በተመድ ዘገባ መሰረት፣ ከመጋቢት 2015 ዓም ወዲህ የሳውዲ ዓረቢያ መራሹ የዓረብ ሃገራት ወታደራዊ ቅንጅት በሁቲ አንፃር ጥቃት ማካሄድ ከጀመረ ወዲህ 7,000 ሰዎች፣ ብዙ ሲቭሎች  ተገድለዋል፣ ሶስት ሚልዮን ደግሞ ሸሽተዋል።

ግሩም ተክለማርያም/አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ