በየመን ጦርነትና አጠያያቂው የኤርትራ ተሳትፎ22 ኅዳር 2008ረቡዕ፣ ኅዳር 22 2008በተመድ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የሶማሊያና ኤርትራ ጉዳይ ተመልካች ኮሚቴ ባለፈው ጥቅምት ወር ባወጣው ዘገባ ኤርትራ በየመን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ለሳኡዲ መራሹ የአረብ ጦር የባህርና የአየር ክልሏን መፍቀዷን ገልጾ ነበር።https://p.dw.com/p/1HG2dምስል Getty Images/AFP/M. Huwaisማስታወቂያ[No title]To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 audio ቢያንስ 400 የሚሆኑ ወታደሮቿን በጦርነቱ ለማሳተፍ ወደ የመን ሳትልክ እንዳልቀርችም በተጨማሪ አስታውቋል። የተመድ የሶማሊያና ኤርትራ ጉዳይ ተመልካች ኮሚቴ ኤርትራ ከሳኡዲ ጋር የጀመረችው ወታደራዊ ትብብር የጸጥታው ምክር ቤት የጦር መሳሪያ ማእቀብ የጣሰ ስለመሆን አለመሆኑ እያጣራ ይገኛል። ናትናኤል ወልዴ አርያም ተክሌ ሸዋዬ ለገሠ