1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዳርፉር ሰላም አስከባሪ ሃይል ላይ የተጣለ ጥቃት

ሰኞ፣ ሐምሌ 8 2005

ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በዳርፉር ፣ ሱዳን ፣ ሰባት የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች መገደላቸዉና ወደ አስራ ሰባት የሚሆኑ ወታደሮች ደግሞ በጠና መቁሰላቸዉ ተነግሮአል። ወታደሮቹ በሙሉ የታንዛያ ተወላጆች እንደሆኑም ታዉቆአል።

https://p.dw.com/p/1981v
ARCHIV - Ein Handout der African Union-United Nations Hybrid Operation in Darfur (UNAMID) zeigt einen bewaffneten Sudanesen am 19.05.2011 nahe Kuma Garadayat, einem Dorf in North Darfur im Sudan. Vieles deutet auf ein unruhiges Jahr auf dem schwarzen Kontinent hin. Schließlich sollen auch in etwa 30 Wahlen über neue Parlamente und Präsidenten entschieden werden. Allerdings ist der Konflikt in Darfur von einer Befriedung weit entfernt. Foto: Albert Gonzales Farran/epa/Handout Editorial Use Only No Sales (Zu dpa-Korr.: «Afrika vor Umbrüchen» vom 20.12.2011) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture alliance / dpa

በምዕራባዊው ሱዳን ክፍለ ሀገር፣ በዳርፉር፣ ይህ የሰላም አስከባሪ ጓድ ተልእኮዉን ከጀመረ፤ ከአምስት ዓመት ወዲህ ከባድ ጥቃት ሲደርስበት የመጀመርያዉ መሆኑም ተነግሮአል፤የ UNAMID ማለት የተባበሩት መንግስታትና የአፍሪቃ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ዉዝግብ ባልተለየዉ የምዕራብ ሱዳን ግዛት ዳርፉር ዉስጥ የተገደሉት ባሳለፍነዉ ቅዳሜ ነበር። ደቡባዊ ዳርፉር ግዛት ኮር አቤቼ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘዉ የጦር ሰፈር የተገደሉት የተባበሩት መንግስታትና የአፍሪቃ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ጓዶች የታንዛንያ ተወላጆች እንደሆኑ ተነግሮአል። የታንዛንያ የግድያዉን ሁኔታ ለማጣራት አንድ የልዑካን ቡድን ወደ አካባቢዉ ላይ መላክዋን የጦር ሃይል ቃል አቀባይ ኮነሪል ካፓባላ ምጋዪ ዛሪ ለዶቸ ቬለ ግልጸዋል፤ የተመ በስፍራዉ ላይ ተጨማሪ የጸጥታ ሰራዊት ማሰማራት እንዳለበት የጠቀሱት የታንዛንያዉ የጦር ሃይል ቃል አቀባይ፤ «የጸጥታ ሃይላቱ የተገደሉበትን ሁናቴ ለማጣራት ልዑካንን ከመላክ ባሻገር በቦታዉ ከመላክ ባሻገር፤ በስፍራዉ ያሉት የፀጥታዉ ሃይላት እንዲህ አይነት አጋጣሚ ላይ ሲወድቁ መቋቋም እንዲያስችላቸዉ የጦር ሃይሉን እንዲጠናከር የተመድ የወታደሩ ቁጥር እንዲጨምር መጠየቅ የሚያስፈልግ ይመስለናል። በሌላ በኩል እንደሚታወቀዉ፤ በቦታዉ ላይ ለጥበቃ የምንጠቀምበት መሳርያ ቀላል አይነት ብቻ ነዉ ምክንያቱም እንዲህ አይነት ሁኔታ ይገጥመናል ብለን አላሰብንም» ባለፈዉ ቅዳሜ በዳርፉር ለደረሰዉ ጥቃት እስካሁን ሃላፊነትን የወሰደ ወገን የለም። በአካባቢዉ ላይ የሚንቀሳቀሰዉ የሱዳን ነጻ አዉጭ ጦር የተሰኘ የዓማጺያን ቡድን በበኩሉ ጥቃቱን ያደረሰዉ ከመንግስት ጋር ሽርክና ያለዉ ሚሊሽያ መሆኑን ማመልከቱ ተዘግቦአል። ይህ ጥቃት በዳርፉር ሰፍሮ ለሚገኘዉ ጦር ምን መልክትን ያስተላልፍ ይሆን በአፍሪቃ ሕብረት ጉዳዮች ላይ ላይ ጥናት የሚካሂዱት ዶክተር መሃሪ ታደለ እንደሚሉት፤ የሰላም ማስከበሩን ተግባር ተግባራዊ ማድረግ አልቻለም።

Peace-keepers with the United Nations-African Union Mission in Darfur (UNAMID) patrol the Shangil Tobaya area for displaced people in North Darfur state, on June 18, 2013. Special envoys to Sudan from the UK, Japan, the UN, as well as UN peacekeeping chief Herve Ladsous and top African Union leaders are holding a retreat in Darfur to review developments over the past two years, as violence worsens. AFP PHOTO/ASHRAF SHAZLY (Photo credit should read ASHRAF SHAZLY/AFP/Getty Images) Erstellt am: 18 Jun 2013
ምስል ASHRAF SHAZLY/AFP/Getty Images

የታንዛንያ የጦር ሃይል ቃል አቀባይ ኮነሪል ምጋዪ፤በዳርፉር በተመ ሰላም አስከባሪ ስር በሚገኘዉ በታንዛንያ የጦር ሰራዊት ላይ በደረሰዉ አደጋ ምክንያት አገራቸዉ በዳርፉር ያላትን የጦር እንደማታሶጣም ተናግረዋል፤ ከዚህ ጥቃት በኋላ ለዓመታት ዉዝግብ ባላጣት ዳርፉር የአፍሪቃ ሕብረት ሀገራት ወታደሮቻቸዉን ለመላክ ዉሳኔ ላይ ይደርሱ ይሆን፤ በአፍሪቃ ሕብረት ጉዳዮች አዋቂዉ ዶክተር መሃሪ ታደለ እንደሚሉት፤ እንብዛም ለዉጥ አያመጣም ባይ ናቸዉ። በሱዳን ዳርፉር የተባበሩት መንግስታትና የአፍሪቃ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ተልዕኮዉን ከጀመረ ይህ ጥቃት ሲደርስ ከአምስት ዓመት ወዲህ ከባዱ መሆኑ ነው። በዳርፉር ሰፍረው የሚገኙት የ UNAMID ሰላም አስከባሪ ወታደሮችና ፖሊሶች ቁጥር 19,700 ግድም እንደሆነ ተገልጾአል።

Soldaten der Rebellenorganisation «Sudanesische Befreiungsarmee» (SLA) patrouillieren in Muhujariya in Süden der sudanesischen Provinz Darfur (Archivfoto vom 25.04.2005). In der westsudanesischen Region Darfur spielt sich seit 2003 eine Tragödie ab. In dem Konflikt zwischen den rebellierenden Stämmen und der Zentralregierung starben bislang nach Angaben des Auswärtigen Amtes schätzungsweise 300 000 Menschen, über zwei Millionen Menschen mussten fliehen. Ein Friedensabkommen zwischen Khartum und der Rebellenorganisation «Sudanesische Befreiungsarmee» (SLA) vom Mai 2006 wurde bereits einen Monat später von den Aufständischen wieder annulliert. Jetzt hat Verteidigungsminister Jung (CDU) erklärt, Deutschland könnte im Rahmen eines UN-Mandats deutsche Soldaten auch nach Darfur entsenden. EPA/khaled el Fiqi (zu dpa 4462) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture alliance/dpa

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ