1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በድርቅ ለተጎዱ ከጀርመን ተጨማሪ ርዳታ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 17 2008

የጀርመን ፊደራል መንግሥት በኤሊንዮ ምክንያት በኢትዮጵያ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖችና በኢትዮጵያ ለሚገኙ ስደተኞች መርጃ የሚዉል ተጨማሪ 13,5 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚሰጥ ተገለፀ።

https://p.dw.com/p/1IcN6
Äthipoien Start deutsch äthiopische Forschungsprojekte in Addis Ababa
ምስል DW/Y. Gebereegeziabeher

ኢትዮጵያን ለሁለት ቀናት የጎበኙት የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና የልማት ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ቶማስ ዚልበርሆርን በተለይ በኢትዮጵያ ኤልኒኞ ባስከተለዉ ድርቅ ሳብያ ለሕፃናትና ለሚያጠቡ እናቶች በተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት በ«ዩኒሴፍ» አማካኝነት አልሚ ምግብ እንዲታደል እንደሚደረግ ተናግረዋል ። ዚልበርሆርን በጉብኝታቸዉ ላይ እንደገለፁት የፖለቲካ ዉሳኔ ሰጭዎች አስቸኳይ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አዜብ ታደሰ

ሒሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ