1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጀርመን የፔጊዳ ንቅናቄና የሰልፉ እገዳ

ማክሰኞ፣ ጥር 12 2007

ትናንት በምስራቅ ጀርመንዋ በድሬስደን ከተማ ፔጌዳ በተባለው ቡድን የተጠራው ና የፔጊዳ ተቃዋሚዎች ሊያካሂዱ ያቀዷቸው ሰልፎች መታገዳቸው እዚህ ጀርመን ማነጋገሩ ቀጥሏል ።እገዳው በጀርመን ሃሳብን በነፃ መግለፅን ተጋፍቷል የሚል ወቀሳ ተሰንዝሮበታል ።

https://p.dw.com/p/1ENQo
PEGIDA und der Alltag der Muslime in Dresden
ምስል DW/K. Salameh

በምሥራቅ ጀርመንዋ በድሬስደን ከተማ ባለፈው ጥቅምት የተጀመረው በጀርመንኛ ምሕጻር «ፔጊዳ» በመባል የታወቀው ጸረ እስልምና ቡድን እንቅስቃሴ በጀርመን አብይ የመነጋገሪያ ርዕስ ከሆነ ሰነበተ። የፔጊዳ ዓላማና የንቅናቄው አካሄድ ማከራከራከሩ ማወቃቀሱ ቀጥሏል ። የቡድኑ ዓላማና የንቅናቄው ዓላማና የደጋፊዎቹ ማንነትም በውይይቶቹ ከሚያነጋግሩት ነጥቦች ውስጥ ናቸው ፍራንክፈርት ጀርመን ነዋሪ የሆኑት የፖለቲካ ሳይንስና የህግ ምሁሩ ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ የፔጌዳን ዓላማ እንቅስቃሴውን እንዲህ ገልፀውታል ።

ከሰሞኑ ስለዚሁ ፔጊዳ የተሰባሰበ መረጃ እንዳመለከተው ቡድኑ በሚካሂዳቸው ሰልፎች ላይ የሚካፈሉት ሰዎች ስብጥር ከሌሎች ተቃውሞች የተለየ ነው ። መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከቀኝ ፅንፈኞችም ጋር በነዚህ ሰልፎች ላይ መካፈላቸው በጀርመን አዲስ ክስተት ሆኖ ተገኝቷል ። ዶክተር ለማ እንደሚሉት ደግሞ የፔጊዳ ዓላማው ግን ግልፅ ሆኖ አያታያቸውም ።

። ፔጊዳ ለ13ተኛ ጊዜ ትናንት በድሬስደን ሊያካሂድ የነበረው ሰልፍ በቡድኑ መሪ ሉትዝ ባህማን ላይ የግድያ ዛቻ መሰንዘሩን የሚጠቁም መረጃ ደርሶኛል ባለው ፖሊስ ታግዷል ። የጀርመን ፖሊስ ያገደው የድሬስደኑን የፔጊዳን ሰልፍ ብቻ ሳይሆን ፔጊዳን በመቃወም በዚያው ከተማ የተጠራውን ሰልፍም ጭምር ነበር ያገደው ። እርምጃው ድጋፍም ተቃውሞም ገጥሞታል ።

PEGIDA Demonstrationen und der Alltag der Muslime in Dresden
ምስል DW/K. Salameh

እገዳው አደጋን ለመከላከል የተወሰደ እርምጃ ነው በሚል ድጋፍ የቸሩት እንዳሉ ሁሉ የሃገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚፈቅደውን ሃሳብን በነፃ መግለፅን ማገድ ነው የሚል ወቀሳም የሰነዘሩበት አሉ ። ዶክተር ለማ ክልከላውን የሚቃወሙትን አስተያየት ነው የሚጋሩት ።

ስደተኞች በብዛት ወደ ጀርመን መግባታቸውን የሚቃወመው ፔጊዳ ባለፈው ሳምንት ባካሄደው 12 ተኛ ሰልፍ 25 ሺህ ሰዎች ተገኝተዋል ። የንቅናቄው ደጋፊዎች መበራከት ትኩረት ስቧል ።ከዚሁ ጋር በዚህችው ከተማ የዛሬ ሳምንት ካሌድ ኢድሪስ ባህሬይ የተባለ አንድ ወጣት ኤርትራዊ በስለት ተገድሎ መገኘቱ ሲያነጋግር ከርሟል ። ፖሊስ ግድያው በመጣራት ላይ መሆኑን አስታውቋል። በከተማይቱ በውጭ ዜጎች ላይ የሚደርሰው ይህን መሰሉ ጥቃት ማስጋቱ አልቀረም ። ዶክተር ለማ መፍትሄው ያለው በሃገሪቱ ህግ ዘንድ ነው ይላሉ ።

በዶክተር ለማ ይፍራሸዋ እምነት የፔጊዳ ንቅናቄ ጠንክሮ የሚዘልቅ አይሆንም ።በዚህ ሳምንት ሰኞ በድሬስደን የፔጊዳ ሰልፍ ቢታገድም ከዓላማው እንደማይደናቀፍ አስታውቋል ።

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ