በጀርመን ጥቁር ፖለቲከኛና ዘረኝነት
ዓርብ፣ መጋቢት 11 2001ማስታወቂያ
ኢብራይሞ አልቤርቶ በትውልድ ሞዛንቢካዊ ሲሆን፤ ሽቬድት በተባለች የምስራቅ ጀርመን አነስተኛ ከተማ ውስጥ ዝነኛ ነው። ታዲያ በከተማው ዝነኝነቱ የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ማለት የSPD ፓርቲ ጥቁር ተወካይ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ ቦክሰኛም በመሆኑ ነው። ኢብራይሞ ከሞዛምቢክ ወደ ቀድሞው የምስራቅ ጀርመን ሲመጣ በቦክሰኝነት ነበር። በርካታ የውጭ ሀገር ነዋሪዎች በከተማዋ የሚገኙ ቀኝ ፅንፈኞችን ፍራቻ አካባቢውን ለቀው ቢሸሹም፤ ኢብራይሞ ግን ዛሬም በዛች ከተማ ነዋሪ ነው።
ማንተጋፍቶት ስለሺ