1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጥቃት የጣለዉ ቱኒዝያዊ ተገደለ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 14 2009

የጀርመን ብሎም የአዉሮጳ የደኅንነት ሰራተኞች በሳምንቱ መጀመርያ ሰኞ ምሽት በርሊን ከተማ በሚገኝ በአንድ የገና ገበያ ላይ በከባድ ጭነት መኪና 12 ሰዎችን ደፍጥጦ የገደለዉና 50 ሰዎችን ለጉዳት የዳረገዉ የ 24 ዓመት ቱኒዝያዊ ሽብርተኛ ጣልያን ሚላን ከተማ ላይ ተገደለ።

https://p.dw.com/p/2UolN
Italien Terrorverdächtiger Anis Amri in Mailand erschossen
ምስል picture-alliance/dpa/D. Bennati/B&V

Q&A_Rome& Berlin/Über Tod des Terrorverdächtigen 'Die akute Gefahr ist beendet - MP3-Stereo

 

አኒስ አምሪ የተባለዉ የ 24 ዓመት ቱኒዝያዉ ስደተኛ ወንጀሉን ለመፈፀሙ ምንም ጥርጥር እንደሌለ ተመልክቶአል። ሽብርተናዉ ተጠርጣሪ መገደሉ እፎይታን ቢሰጥም ፤እሱን ይረዱ የነበሩ ሰዎች መኖራቸዉ የማያጠያይቅና እነዚሁ ሠዎች አደናዉ መቀጠሉ ተመልክቶአል።

ተጠርጣሪዉ የቱኒዚያ ዜጋ አኒስ አምሪ በሁለት የጣሊያን ፖሊሶች ከሌሊቱ 9 ሰዓት ላይ መታወቂያ ሲጠየቅ ሽጉጥ አዉጥቶ አንደኛዉን በማቁሰሉ እዚያዉ በጥይት መገደሉ ነዉ የተገለጸዉ። የጣሊያን የሀገር ዉስጥ ሚኒስትር ማርኮ ሚኒቲ፤

Fahndung nach Anis Amri
ምስል Reuters

 «ዛሬ ሌሊት በ9ሰዓት ላይ ሚላን፤ ሴስቶ ሳን ጆቫኒ ባቡር ጣቢያ መደበኛ ቁጥጥር ሲካሄድ ለዚህ ተግባር የተሰማሩ ፖሊሶች ጥርጣሬ የፈጠረባቸዉን አንድ ሰዉ ያስቆማሉ። ግለሰቡ ወዲያዉ ሽጉጡን አዉጥቶ ሳያመነታ መታወቂያ ወደጠየቀዉ ፖሊስ ላይ ይተኩሳል። ፖሊሱ ክርስቲያን ማቪዮ ይባላል። ለጥበቃ የተሰማራዉ ፖሊስም ወዲያዉ አፀፋዉን መለሰ። እንደእድል ሆኖ ክርስቲያን ማቪዮ የሚያሰጋ ቦታ ላይ አልተመታም። ሃኪም ቤት ገብቶ በማገገም ላይ ነዉ፤ ሁኔታዉም ለሞት አያሰጋም።»

ተጠርጣሪዉ በርሊን ላይ አደጋዉን ካደረሰ ወዲህ ለቀናት በመላዉ አዉሮጳ ሲፈለግ ቆይቷል። ግለሰቡ በፈረንሳይ በኩል ወደ ጣሊያን እንደተጓዘ ከተሰማ በኋላም የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት ድንበር ክፍት መሆን የለበትም የሚሉት ወገኖች ትችታቸዉን አጠናክረዋል። መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የጥገኝነት ጥያቄያቸዉ ተቀባይነት ያላገኘ የቱኒዚያ ዜጎችን ወደሃገራቸዉ የመመለሱ ርምጃ እንዲፋጠን ለቱኒዚያ ፕሬዝደንት ማሳሰቢያ አቅርበዋል። ስለተጠርጣሪዉ መገደልና የፖለቲከኞች አስተያየት የበርሊንና የሮም ወኪሎቻችን በስልክ ጠይቀናል።

ተክለዝጊ ገ/እየሱስ

ይልማ ኃይለሚካኤል 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መኃመድ