1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጂዳ፣ የኢትዮጵያዊቷ በደልና እሥራት፣

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 6 2002

ድኅነት በራስ ላይ ከሚያደርሰው ሰቆቃ ባሻገር፣ ለውርደት እንደሚያደርግ የታወቀ ነው። በድኅነት ሳቢያ ሥራ ለማግኘት ወደተለያዩ አገሮች የሚጓዙ ኢትዮጵያውያት

https://p.dw.com/p/L3F2
ምስል dpa

የተለያዬ አሠቃቂ ችግር እንደሚያጋጥማቸው በየጊዜው የሚሰማ ጉዳይ ነው። በስዑዲ ዐረቢያ ፣ በ ዐረብ ዓሚሮችኅብረትም ሆነ በሊባኖስ በሚደርስባቸው ግፍ ሳቢያ፣ አንዳንዶቹ፣ የራሳቸውን ህይወት እስከማጥፋት መድረሳቸው ይሰማል። ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ፣የሚወጡትን መርዳቱ ያስቸግራል ቢባልም እንኳ፣ በህግ ታውቀው ተመዝግበው ለሥራ የተሠማሩ ዜጎችጩ አላግባብ በደል ሲደርስባቸው ፣ የትውልድ አገራቸው ኤምባሲም ሆነ ቆንስል ፈጥኖ ሊደርስላቸው ይገባል፣ በጂዳ ፣ አንዲት ኢትዮጵያዊት ድርብርብ የሆነ ከባድ ችግር የደረሰባት ከመሆኑም በአሥር ቤት 3 ወራት በመማቀቅ ላይ ትገኛለች። ነቢዩ ሲራክ፣ ጉዳይዋን ተከታትሎ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።

ነቢዩ ሲራክ

ተክሌ የኋላ/ሒሩት መለሰ