1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጄዳ የኢትዮጵያ ዓ/ዓቀፍ ት/ቤት ችግር

ሰኞ፣ የካቲት 3 2006

በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳጊ ኢትዮጵያዉያን እንደሚማሩበት የሚገለፀዉ በጅድ የኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ ትምህርት ቤት ከተመሠረተ ከ15ዓመታት በላይ እንደሆነዉ ይነገራል።

https://p.dw.com/p/1B6Qg
Buchveröffentlichung in Kabul
ምስል DW/H. Sirat

በተቃራኒዉ ትምህርት ቤቱ ከተቋቋመ ቢቆይም የራሱ የሆነ የማስተማሪያ ሕንፃ እንደሌለዉ ነዉ የጅዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ በላከዉ ዘገባ ጠቅሷል። ሰሞኑን ደግሞ በሥራና የመኖሪያ ፈቃድ አለመስተካከል ምክንያት የትምህርት ቤቱ 25 መምህራን ሥራ ለማቆም እንደሚገደዱ ያመለከቱ ሲሆን ፈቃዳቸዉም ባስቸኳይ እንዲስተካከል ነዉ ያሳሰቡት። ሰሞኑን የትምህርት ቤቱ የወላጅ መምህራን ህብረት ስብሰባ ያካሄደ ሲሆን አሉ የተባሉ ችግሮችን በዝርዝር በማቅረብ ተወያይተዋል።

ነቢዩ ሲራክ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ