1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጎርፍ ሳቢያ ግማሽ ሚሊዮን ኢትዮዽያዊ አደጋ ውስጥ ነው--- ኦቻ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 25 2002

በሰሜን ምዕራብ ኢትዮዽያ በአማራ ዝቅተኛ በሆኑ አከባቢዎች እየጣለ ባለው ዝናብ የተነሳ በደረሰው የ ጎርፍ አደጋ ህይወትና ንብረት ጠፍቷል። ዝናቡ በዚሁ ከቀጠለ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኢትዮዽያዊ አደጋ ውስጥ ይገባል።

https://p.dw.com/p/P0tT
ምስል AP

የክረምቱ ዝናብ ህይወት እያጠፋ፤ ንብረት እያወደመ ነው። ባለፈው ሳምንት በደረሰው የጎርፍ አደጋ የ19 ሰዎች ህይወት ጠፍቷል። 12 ሺህ ሰዎች ተፈናቅለዋል። በተለይም በአማራ ብሄራዊ ክልል ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች መስሪያ ቤት የኢትዮዽያ ቅርንጫፍ(ኦቻ) ይፋ ያደረገው ሪፖርት አንደሚያሳየው የክረምቱ ዝናብ በዚሁ ከቀጠለ ከ270 ሺህ በላይ ሰዎች ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል። መንግስት አሀዙን በ100ሺህ ዝቅ አድርጎ 153 ሺህ ኢትዮዽያን በመጪዎቹ ጊዜያት በጎርፍ ሳቢያ አደጋ ላይ እንደሚወድቁ ገልጿል። የኦቻ የኢትዮዽያ ዳይሬክተር ቪንሴንት ሌሌይ ለዶቸቬሌ እንደገለጹት ወንዞች አከባቢ የሚኖሩ ሰዎች ክፉኛ እየተጎዱ ናቸው። ኦቻ አደጋውን ለመከላከል 6ነጥብ8 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ገልጿል።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ