1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጎ ፍቃደኛ የእግር ኳስ አሰልጣኞች

ዓርብ፣ ኅዳር 6 2006

ያለንን ችሎታ ማካፈል እንፈልጋለን ይላሉ። ችሎታቸውም እግር ኳስ መጫወት ነው።

https://p.dw.com/p/1AHf3
***Achtung: Nur zur mit Christian Mamo abgesprochenen Berichterstattung verwenden!*** Mekdela Fußball Team - Seit einem Jahr trainiert Christian Mamo mit Jugendlichen Fußball in Addis Abeba. *** Datum: 14.11.2013 Bildrechte : Christian Mamo
ምስል Christian Mamo

እግር ኳስ ኃብታም ወይም ደሀ ፤ ጥቁር ወይም ነጭ አይልም። የቻለ በስታዲዮም ያልቻለ በአፈር ሜዳ ላይ፤ ያለው በመደበኛ የሌለው በጨርቅ ኳስ ይጫወታል።

ለእግር ኳስ በብዙዎች ዘንድ የሚዘወተርና የሚወደድ ጨዋታ ነው። ክርስትያን ማሞ የእግር ኳስ ፍቅር ብቻ ሳይሆን የሚያውቀውን የእግር ኳስ አጨዋወት ደንብ እና ስልትን ለሌሎች ማካፈል ከወሰነ አንድ አመት ሆኖታል። ክርስትያን በአዲስ አበባ መኖር ከጀመረ ሰባት አመቱ ነው። ከዛ በፊት ወላጆቹ በስራ ምክንያት በተለያዩ ሀገራት መኖር ስለነበረባቸው በአምስት ሀገራት ነው ያደገው።

Die Rechte wurden uns vom DW Korrespondent in Bissau (Guiné-Bissau), Braima Darame erteilt. Zulieferer: Maria João Pinto (Portugiesisch fur Afrika) Titel: Neighbourhood Soccer Championships Guinea Bildbeschreibung: Children playing soccer in "Rua Paz", in the Militar Neighbourhood in Bissau Fotograf: Braima Darame (DW Korrespondent) Wann wurde das Bild gemacht: 26.08.2013 Wo wurde das Bild aufgenommen: Bissau (Guiné-Bissau) Schlagwörte: Children, Guinea-Bissau, Soccer
የጊኒ ቢሳው ታዳጊዎች የእግር ኳስ ጨዋታ ሲለማመዱምስል DW/B. Darame

ክርስቲያን ሌሎች ወጣቶችን የእግር ኳስ ጨዋታ ለማሰልጠን ከዓመት በፊት ሲነሳሳ ሀሳቡን ያጋራው ለትምህርት ቤት ጓደኛው ቀና ሳምሶን ነው። ቀና ዛሬ ከክርስትያን ጋር አብሮ ወጣቶች ያሰለጥናል። ሌሎችን ለመርዳት የተነሳሱት የእግር ኳስ አሰልጣኞቹ እና ሰልጣኞቹ እግር ኳስ የሚጫወቱ ከትምህርት ቤት መልስ ነው። ሁለቱም በግል ስለሚንቀሳቀሱ ብዙ ወጣቶችን በቡድናቸው ሊያቅፉ አልቻሉም። ስለሆነም ለቡድኑ አባላት አመራረጥ የራሳቸውን መስፈርት አስቀምጠዋል።

ከሰልጣኞቹ አንዱ የማነ ገብረ መድህን ይባላል። የ9ኛ ክፍል ተማሪ ነው። የማነ አጥቂ ነው ። ከልጅነት ጀምሬ እግር ኳስ እጫወታለሁ የሚለው የማነ በዚህ ቡድን ውስጥ መሰልጠኑ እንደጠቀመው ይናገራል።

አንድ ቀን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመጫወት ተስፋ ያላቸው አንድ ሶስት ልጆች አሉን ይላል ቀና። ክርስትያን ደግሞ ይህንን ዕድል የሚያገኙበትን መንገድ እያመቻቸ ይገኛል። ስለክርስትያን እና ቀና የበለጠ ከድምፅ ዘገባው ያገኛሉ።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ