1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በ 2 ተኛው የዓለም ጦርነት የ 3 ተኛው ዓለም ሚና

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 6 2003

60 ሚሊዮን ሰዎች እንዳለቁ ከሚገመትበት የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ታሪክ አንዳንዱ ክፍል በአብዛኛው በምዕራቡ ዓለም ፈፅሞ አይታወቅም ። በምዕራባውያኑ ታሪክ ከተመዘገበው የተወሰነውም የተዛባ ሲሆን አንዳንዱም ሆን ተብሎ ተድበስብሶ እንዲታለፍ ተደርጓል ።

https://p.dw.com/p/QYfd
ምስል Ria Novosti/ICRC
ከዚህ ውስጥ በጦርነቱ የ 3 ተኛው ዓለም በተለይም የአፍሪቃውያን ሚና አንዱ ነው ። ከመስከረም አንስቶ በምዕራብ ጀርመኗ የኮሎኝ ከተማ በመታየት ያለ አንድ ዐውደ ርዕይ ይህን የተሳሳተና በርካታ አውሮፓውያን የማያውቁትን የተደበቀ ታሪክ ያሳያል ። “በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የ 3 ተኛው ዓለም ሚና“ የተሰኘው ይህ ዐውደ ርዕይ የቀረበበት ህንፃም በጦርነቱ የናዚ ጀርመን ቁምስቅል ማሳያ ስፍራ ነበር ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን እዚህ አውሮፓ ብዙም በማይታወቀው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የአፍሪቃውያን ድርሻ ላይ ያተኩራል ። አብረን እንቆይ ። ሂሩት መለሰ ተክሌ የኋላ