1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 በ2017 የታሰሩ ጋዜጠኞች ብዛት

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 4 2010

አምና በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪቃ የሰወስተኝነቱን ደረጃ ይዛ የነበረችዉ ኢትዮጵያ ዘንድሮ ደረጃዋን ለሌላ ለቅቃለች።

https://p.dw.com/p/2pJiq
Logo CPJ
ምስል APTN

(Beri.WDC) CPJ Bericht - MP3-Stereo

ባገባደድነዉ የጎርጎሪያን 2017 ዓመት የታሰሩት ጋዜጠኞች ቁጥር አምና ታስረዉ ከነበሩት መጨመሩን CPJ በሚል ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ አስታወቀ። ኮሚቴዉ  ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ዓመታዊ ዘገባዉ እንዳስታወቀዉ ዘንድሮ በመላዉ ዓለም የታሰሩት ጋዜጠኞች 262 ናቸዉ። አምና በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪቃ የሰወስተኝነቱን ደረጃ ይዛ የነበረችዉ ኢትዮጵያ ዘንድሮ ደረጃዋን ለሌላ ለቅቃለች። ግብፅ እና ኤርትራ ግን በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ዘንድሮም እንዳምናዉ የመጀመሪያ እና ሁለተኛዉን ሥፍራ እንደያዙ ናቸዉ። የዋሽግተን ዲሲ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ