በ2017 የጀርመን የአፍሪቃ ፖለቲካ ትኩረት  | አፍሪቃ | DW | 29.12.2016

አፍሪቃ

በ2017 የጀርመን የአፍሪቃ ፖለቲካ ትኩረት 

2017 የጀርመን ምክር ቤት አባላት ምርጫ የሚካሄድበት በመሆኑ ፖለቲከኞች ከውጭ ይልቅ የሀገር ውስጥ ፖለቲካ ላይ ነው ትኩረታቸው ።የሀገር ውስጥ ፀጥታ የጡረታ እና የጤና ጉዳዮችን የመሳሰሉት የመነጋገሪያ አጀንዳዎች ይሆናሉ ። ሆኖም የ2017 የቡድን ሀያ ጉባኤ አስተናጋጅ ጀርመን በዓመቱ የአፍሪቃ መንግሥታትን የሚያሳትፍ ልዩ ጉባኤ ጠርታለች ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:07

የጀርመን የአፍሪቃ ፖለቲካ ትኩረት 

ሊብት ጥቂት ቀናት በቀሩት በጎርጎሮሳዊው 2017 ዓም ጀርመን አገር ዓቀፉ ምርጫ ላይ የምታተኩር ቢሆንም የአፍሪቃ ልማት ጉዳይ ከአጀንዳዎቿ አንዱ እንደሆነ በቅርቡ አስታውቃለች ።የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በጎርጎሮሳውያኑ ህዳር መጨረሻ ባስተላለፉት የቪድዮ መልዕክት በዓመቱ በአፍሪቃ ልማት እንዲፋጠን መንግሥታቸው ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል ።
«በመጀመሪያ ደረጃ ከተለመደው የልማት እርዳታ ጎን ለጎን የአፍሪቃን ኤኮኖሚ ማሳደግ በምንችልበት የተሻሉ መንገዶች ላይ በአንድ ላይ እንመክራለን ።ያ ማለት ከአፍሪቃ የልማት ባንኮች ጋር የትኛዎቹን የትብብር መስኮች ይበልጥ ማጠናከር እንችላለን ? በአፍሪቃ መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች እንዴት መርዳት እንችላለን ? በሚሉትን ጥያቄዎች ላይ ነው የምንመክረው ። እዚህም ላይ ከጀርመን የገንዘብ ፣ የኤኮኖሚ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አንስቶ እስከ የውጭ እና የልማት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች  ድረስ እኔን ጨምሮ ማለት ነው በአጠቃላይ መንግሥታችን በጋራ እሰራለን ። »
ሜርክል ያሉት እንዴት በሥራ እንደሚተረጎም በጎርጎሮሳዊው 2017 ጀርመን ስለ ምታስተናግደው የቡድን ሀያ ጉባኤ በጀርመን ፌደራል መንግሥት የተዘጋጀ አንድ ሰነድ ላይ ሰፍሯል ።

Deutschland Berlin - Gedenken für die Opfer der deutschen Kolonialherrschaft (picture-alliance/dpa/S. Pilick)

በዓመቱ በአፍሪቃ ለግል ባለሀብቶች ፣ ሁኔታዎችይበልጥ እንዲሻሻሉ እና ለመሠረተ ልማት ግንባታ ተጨማሪ ገንዘብ መመደብ እንደሚያስፈልግ ሰነዱ ያስረዳል ። የጤና አገልግሎቶችን ማሻሻል ፣ የስደት ምክንያቶችን ማድረቅ ፣ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን ተጽእኖዎች ማስቆም ከተያዙት ግቦች ውስጥ ይካተታሉ ። በነዚህ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው የጀርመን እና የአፍሪቃ  አጋርነት ልዩ ጉባኤ በርሊን ውስጥ በመጪው ሰኔ ይካሄዳል ። ይሁንና ከወዲሁ ስለ ጉባኤው የተነገሩት ተስፋ ሰጭ መግለጫዎች ተግባራዊ ይሁኑ አይሁኑ ማንም አያውቅም ።እስከ ዛሬ ከአፍሪቃ ጋር ትብብሮችን ለማጠናከር የሚተላለፉ የዓለም ዓቀፍ ውሳኔዎች እጥረት የለም ።ለምሳሌ ጂ8 የሚባለው በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ሀገራት ቡድን በ2005 ግሌንኢግልስ ስኮትላንድ ባካሄደው የልማት ጉባኤ፣መንግሥታት ለአፍሪቃ የሚሰጡትን የልማት እርዳታ እስከ ጎርጎሮሳዊው 2010፣ በ25 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ ቃል ገብተው ነበር ። ይሁንና መንግሥታት የሚያጋጥሟቸውን ኤኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና አስተዳደራዊ ተግዳሮች እንዲወጡ እገዛ የሚያደርገው በምህፃሩ OECD የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት

Deutschland Auftakt der deutschen G20-Präsidentschaft 2017 (picture alliance/dpa/B. von Jutrczenka)

እንደሚለው ቃል ከተገባው ገንዘብ አፍሪቃ ያገኘችው ከ 11 ቢሊዮን ዶላር አይበልጥም ።አንዳንድ ለጋሽ ሀገራት ቃላቸውን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አላደረጉም ። ከመካከላቸው አንዷ ጀርመን ናት ። በ2017 አስቸጋሪ ይሆናል ተብሎ የሚገመተው ከናሚብያ ጋር የሚካሄደው ንግግር ነው ።ጀርመን ናሚብያን ቅኝ በገዛችበት ከጎርጎሮሳዊው 1904 እስከ 1908 ተፈፅሟል ለተባለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ይቅርታ መጠየቅ ትፈልጋለች ። ሁለቱ ሀገራት በዚህ ጉዳይ ላይ በ2016 መጨረሻ አንድ ውል ሊፈራረሙ አቅደው ነበር ። ሆኖም ጀርመን እና ናሚብያ የሚያካሂዱት ውይይት የጀርመን ልዩ ተወካይ ሩፕሬሽት ፖሌንዝ እንዳሉት ስምምነቱ በታቀደው ጊዜ ተግባራዊ አይሆንም ።
« ተግባራዊ ሊሆን የሚችልበትን ጊዜ ለመያዝ አቅደን ነበር ። ሆኖም በዚህ ዓመት መጨረሻ ልናደርገው አልቻልንም ። ይህ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ አይደለም ። ይልቁንም ምን ያህል ጊዜ እንደሚያስፈልገን የቀረበ ሀሳብ እንጂ ። አሁን ለስምምነቱ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገናል ።» 
ከዚህ ሌላ በአደገኛው የማሊ የተመድ ተልዕኮ የሚሰማሩት የጀርመን ወታደሮች ቁጥር ላይ የጀርመን ካቢኔ  በ2017 መጀመሪያ ላይ ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል ።

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ 
 

Audios and videos on the topic

Albanian Shqip

Amharic አማርኛ

Arabic العربية

Bengali বাংলা

Bosnian B/H/S

Bulgarian Български

Chinese (Simplified) 简

Chinese (Traditional) 繁

Croatian Hrvatski

Dari دری

English English

French Français

German Deutsch

Greek Ελληνικά

Hausa Hausa

Hindi हिन्दी

Indonesian Bahasa Indonesia

Kiswahili Kiswahili

Macedonian Македонски

Pashto پښتو

Persian فارسی

Polish Polski

Portuguese Português para África

Portuguese Português do Brasil

Romanian Română

Russian Русский

Serbian Српски/Srpski

Spanish Español

Turkish Türkçe

Ukrainian Українська

Urdu اردو