1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቡሩንዲ የተቃዉሞ ሠልፍ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 20 2007

የቡሩንዲ መንግሥት የግል ራዲዮ ጣቢያዎችንና ጋዜጠኞችን ዘግቷል።ዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ሕብረት የቡሩንዲ መንግሥት የሕዝቡን መብት እንዲያከብር ሲጠይቁ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ደግሞ ልዩ መልዕክተኛቸዉን ወደ ቡጁምቡራ ልከዋል።

https://p.dw.com/p/1FGO1
ቡሩንዲ የተቃዉሞ ሠልፍ
ምስል Reuters/T. Mukoya

የቡሩንዲ ፕሬዝደንት ፔሪ ንኩሩንዚዛ የሐገሪቱ ሕገ መንግሥት ከሚፈቅደዉ ዉጪ ለሰወስተኛ ዘመነ-ሥልጣን ለመወዳደር መወሰናቸዉ ያስቆጣዉ የሐገሪቱ ሕዝብ በሳምንቱ ማብቂያ የጀመረዉ የአደባባይ ሠልፍ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።ባለፈዉ ዕሁድና ሰኞች ርዕሠ-ከተማ ቡጁምቡራ አደባባይ የወጣዉ ሠልፈኛ ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ተጋጭቶ በትንሹ አምስት ሰዎች ተገድለዋል፤በመቶ የሚቆጠሩ ቆስለዋል፤ ሌሎች ታስረዋል።የቡሩንዲ መንግሥት የግል ራዲዮ ጣቢያዎችንና ጋዜጠኞችን ዘግቷል።ዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ሕብረት የቡሩንዲ መንግሥት የሕዝቡን መብት እንዲያከብር ሲጠይቁ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ደግሞ ልዩ መልዕክተኛቸዉን ወደ ቡጁምቡራ ልከዋል።ከብሩንዲ ለደረሰንን ዘገባ ጥንቅር የበርርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ