1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቡናና ልዩ ልዩ ጠቀሜታው፣

ረቡዕ፣ ሐምሌ 3 2005

ጀርመን በቢራ ዓይነት የታወቀ ሀገር ነው ፤ በብዛትም ይጠጣል፤ በዓመት በነፍስ ወከፍ ሲሰላ እያንዳንዱ ሰው 112,5 ሊትር ያህል ቢራ ይጠጣል ማለት ነው። ትኩሱ መጠጥ ቡና ደግሞ ፣ አሁንም ከዚያ ልቆ ፣ የአንደኝነቱን ሥፍራ እንደያዘ ነው ።

https://p.dw.com/p/195uP
ምስል CC/James Gagen

በዓመት፤ በአማካይ 149 ሊትር ነው የሚጠጣው። ከዩናይትድ እስቴትስና ብራዚል ቀጥላ በ3ኛ ደረጃ ፣ ቡና በብዛት የሚሸጥባትም ሆነ የሚጠጣባት ሀገር ፣ ጀርመን ናት። በቡና ጭምቆ የታወቀችውን ሀገር ኢጣልያንን ጭምር ጀርመን በ 10 ከመቶ ትበልጣለች።

Kaffeebohnen werden zum Trocknen in der Sonne ausgebreitet
ምስል picture-alliance/dpa

በዓለም ፣ ቡና በሰፊው በምማረት የታወቁት፤ ብራዚል ቪየትናም ኮሎምቢያ ፣ ከአፍሪቃም በ3ኛነት ደረጃ ኢትዮጵያ ትገኛለች።

ቡና በሚያመርቱና በሚሸምቱ አገሮች ፣ ለዚህ ተወዳጅ መጠጥ የሚሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ነው። በዚህ በጀርመን ሀገር፤ በተለይም በቦን ዩንቨርስቲ የልማት ምርምር ማዕከል የተሰኘው ድርጅት፤ የኢትዮጵያ ቡና በተለይ ወፍ ዘራሹ ፣ ወይም በተፈጥሮ በጫካ በቅሎ የሚገኘው፤ በህዝብ ብዛት ሳቢያ መሬት ለእርሻ ተፈላጊ ነው ተብሎ ደን በብዛት ሲመነጠር ወፍ ዘራሹ ቡናም ተመሳሳይ ዕጣ ስለሚያጋጥመው ፤ ይህ እንዳይሆን የበኩሉን አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ በየጊዜው ይገልጻል።

ብርቁ የዛፍ ፍሬ ፤ እጅግ ተፈላጊ እንደመሆኑ መጠን፣ ምርቱ፣ ጥራቱን ጠብቆ ለገበያ እንዲቀርብ፤ ለአምራች ገበሬዎች፤ ለነጋዴዎች፣ ለመንግሥትም በገቢ ረገድ ጥቅም እንዲሰጥ ፣ በተለያዩ ሙያዎች የሠለጠኑ ሰዎች ፤ ከቡና ጋር የተያያዙ ኩባንያዎች፤ የጥራት ተቆጣጣሪ ድርጅቶች አቋቋመው የበኩላቸውን ተግባር ያከናውናሉ።

ከተለያዩት ኩባንያዎች አንዱ፣ ለቡና ጥራት የራሱ ቤተ-ሙከራ (ላቦራትሪ)ያለው «ሜታድ /ካቡ የቡና ጥራት መቆጣጠሪያ ቤተ ሙከራ»የተሰኘው ኩባንያ ነው።

ስለ ቤተ ሙከራው ተግባር፣ ዋናው ሥራ አስኪያጅ አቶ አማን አድነው----

Bildergalerie Bioanbau in Uganda Wildkaffee
ምስል DW/L. Schadomsky

«ዐረቢካ » በሚል ሥያሜ የታወቀው «ኢቲዮፒካ« መባል ይገባው የነበረው የኢትዮጵያ ቡና፣ «ሮቡስታ» የተሰኘው ሌላው የቡና ዓይነትም ቢሆን ከማንቃትም ሆነ ዘና ከሚያደርገው ባህሪያቸው ሌላ ፣ ላቅ ያለ ጠቀሜታ እንዳላቸው በየጊዜው ከሚካሄዱ የምርምር ውጤቶች እንከታተለን። ቡና አነቃቂ ብቻ ሳይሆን፣ ለጤንነትም የሚበጅ ነው የሚሉት ፣ ጀርመናዊው ፕሮፌሰር፣ ዶ/ር ዩስቱስ ማየር ፣ ቡና፣ ሰውነት ውስጥ እባጭ ሲያጋጥም ሠርሥሮ ገብቶ፣ የካንሠር /ነቀርሳ አዛማች ኅዋሳትን እየታገለ ያስወግዳል። በቀን ሦስት ስኒ (ፍንጃል)ቡና መጠጣት፣ የኩላሊት ካንሠር አደጋ እንዳይከሠት ይረዳል ይላሉ። የጣፊያን፣ አንጀትንና የቆዳ ካንሠርንም በተመሳሳይ ሁኔታ ይታገላል።

ዶ/ር ማየር፤ ቡና በደም ውስጥ ስኳር እንዳይበዛ፤ እንዲቀነስ የሚያደርግ የራሱ ቅመም እንዳለውም አስገንዝበዋል።

በደም ውስጥ የምግብ ቅባት መብዛትን ይከላከላል፣የደም መተላለፊያ መስመሮች እንዳይጎዱ ያግዛል በቡና ላይ ወትት ፣ የወተት አረፋ ወይም «ክሪም» መጨመሩ ግን ፣ አዎንታዊውን ውጤት አሉታዊ ያደረገዋል ነው ያሉት።

ከዚህም ሌላ በእርጅና ሳቢያ የሚከሠቱ መዘንጋትን የመሳሰሉ እክሎችንም ቡና ይከላከላል እንደ ዶ/ር ዩስቱስ ማየር አገላለጽ!።

ይህ የአንድ ተመራማሪ የጥናት ውጤት ነው። ለህክምና ፤ ከሃኪም እንደሚታዘዝ ክኒን ሊቆጠር ስለማይገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ሀኪምን ማመከር ተገቢ ይሆናል ብለን እናምናለን።

ስለቡና ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ፣አቶ አማን አድነው---

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ