1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባህላዊ መጠሪያዎችና ፍቻቸዉ

Azeb Tadesseቅዳሜ፣ ሐምሌ 18 2001

በኢትዮጽያዉያን ባህል ስም ለሰያሚዉም ለተሰያሚዉም የተለያዩ ሚናዎችን የሚጫወት ትርጉም አዘል ቃል ነዉ። በተለይ በጎጃም አካባቢ የልጅ እና የአባት ስም በአብዛኛዉ የገላጭ እና የተገላጭ ጽንሰ ሃሳብ ይይዛል።

https://p.dw.com/p/IxOl
ምስል British Museum
ወደ መሃል አገር ወደ ሸዋ አካባቢ በአብዛኛዉ የጀግንነት ሁኔታን የሚገልጹ ስሞችን እናገኛለን። ለምሳሌ ደባልቄ፣ ለጥይበሉ የመሳሰሉ ስሞችን። ሌላዉ ሰያሚዉ የደረሰበት ታሪክ ለማዉሳትም ለስምነት ይጠቅምበታል። ለምሳሌ አቶ ተክሉ በወጣትነት እድሚያቸዉ ትምህርት እንዳጠናቀቁ በድንገት በበጋ ወቅት ሴት ልጅ ቢወልዱ፣ በበጋ ወር እሸት አይለቀምም፣ እኔ ግን በበጋ ወቅት ያገኘሁሽ እሸቴ ነሽ ሲሉ ልጃቸዉን የበጋእሸት ተክሉ ብለዉ ሰይመዋታል።
የታዋቂዉ ኢትዮጽያዊ ደራሲ የበአሉ ግርማ አብሮ አደግ ጓደኛ አቶ ታደሰ ደግሞ የጓደኛቸዉ የአቶ በአሉ ግርማ በድንገት መሰወር ልባቸዉ ቢነካ ወንድ ልጅ ሲወልዱ ለደራሲዉ ማስታወሻ ብለዉ ልጃቸዉን ከአድማስ ባሻገር ታደሰ ብለዉታል። ስለ አገራችን ባህላዊ እና ዘመናዊ የስም አወጣጥ በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ በቋንቋዎች ጥናት ማዕከል የስነ-ልሳን መምህር ከአቶ ሙሉሰዉ አስራቴ ጋር ቆይታ አድርገናል ያድምጡ